የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጥገናና ለስልጠና ግብዓት የሚሆኑ የብረታ ብረትና እንጨት ሥራ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳትና የከፊል ቋሚ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክና የአውቶ መካኒክ ስልጠና ዕቃዎች እንዲሁም ለልብስ ስፌት ስልጠናና ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ጨርቃ ጨርቅና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለጥገናና ለስልጠና ግብዓት የሚሆኑ የብረታ ብረትና እንጨት ሥራ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳትና የከፊል ቋሚ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክና የአውቶ መካኒክ ስልጠና ዕቃዎች እንዲሁም ለልብስ ስፌት ስልጠናና ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚውሉ ጨርቃ ጨርቅና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 20, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት

  • ለጥገናና የስልጠና ግብዓት ለብረታ ብረትና እንጨት ስራ፣
  • የፅህፈት መሣሪያ፣ ለፅዳትና ለከፊል ቋሚ ዕቃዎች
  • ለኤሌክትሪክና ለአዉቶመካኒክ ሥልጠና፣
  • ለልብስ ስፌት ሥራ ስልጠናና ለደንብ ልብስ አገልግሎት የሚዉሉ ጨርቃ ጨርቅና ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡–

ከላይ የተገለፁትን ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩትን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ መደረጉን የሚያረጋግጡ መረጃዎች፤ የዕቃ(የአገልግሎት) አቅራቢዎች ምዝገባ ስለመታቀፋቸዉ ከንግድ ሚንስቴር የተሰጣችሁን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም ከግዥ ኤጄንሲ በተለቀቀ የመረጃ መረብ ውስጥ ተመዝግበው የሚገኙ እንዲሁም የሀገር ዉስጥ ገቢ ባለስልጣን ጨረታ ላይ ለመሳተፍየሚያስችል የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ህጋዊ ማስረጃዎችን ለዚህ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባችኋል።

ስለሆነም፡–

  1. ተጫረቾች የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት የቴክኒክና የዋጋዉ ሰነድ በአንድ ኢንቨሎፕ በማድረግና በማሸግ በግልፅ በፖስታዉ ላይ በመፃፍና በመፈረም ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀዉ ሣጥን ዉስጥ በታሸገዉ ፖስታ ማስገባት አለባችዉ።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10(አስር) ቀን በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት በድሬ ዳዋ ማ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 311 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ በተረጋገጠ CPO ዋይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና መጠን፣ጨረታዉ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በተመለከተ እንዲሁም ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን በጨረታ ሰነድ ዉስጥ ያገኙታል።
  5. ተጫራቾች ሰነዶችን ለማስገባት ሲመጡ ስለሚጫረቱባቸዉ የዕቃዎች ናሙና አብረዉ ማቅረብ አለባቸዉ።
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም የቴክኒካልና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነዱ በመ/ቤታችን በተባለው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን

የድሬ ዳዋ ሁሉ አቀፍ ማረሚያና ማረፊያ ቤት