በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶችን መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ-16 /2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም

  • ac adaptor, hd tv cable tv wall mount led highbay light skmei iron adult hand watch wooden door frame & water purifier out door solar stright light & stright light stand led string lights፣ 
  • rubber nail filter, s/s manicure, metal decorative & eye lash፣
  • photo copy machine and printer adult fabric cap, shopping bag & others rechargeable camping portable shower፣
  • wall transformer፣
  • chemical mixing tank, channel steel, galvanized steel pipe heald frame: fabric micro fiber cleaning towel single, double port face plate & other s/s artificial earring & bearing, school bag, fabric adult cap & supermarket shelf childred sport shoes brand & lady sport shoes brand: lady skirt, lady tight & other vibration analysis of centerfugal blower fan mobile screen protection glass ፣
  • electric crane scale፣
  • hair cliper perfume & trouser፣ 
  • touch screen oca glass m-triangle led screen defoaming machine with bubble remover & others two side coated art papers፣
  • የስቴሽነሪና ማስታወቂያ እቃዎችና
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል።
  2.  ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆነ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ። 
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ በኦንላይን የአክሽን ኢትየጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች በወረቀት የሚያለያዘ ከሆነ የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ  ጽ/ቤቱ ሥም  ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ  ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
  4. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የኦክሸን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  7. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
  8. በተራ ቁጥር 07 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
  9. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
  10. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55 11/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡።
  12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ወይም 022-236-0190 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በጉምሩክ ኮሚሽን   የሞጆ ጉ/ ቅ/ ጽ/ ቤት