Addis Zemen (Nov 05, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ-09/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ንብረቶች (ለአልሙኒየም እና ለብረታ ብረቶች አቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ) ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
|
1 |
ቁርጥራጭ ብረቶች |
ኮተቤ መካኒካል ወርክ ሾፕ ግቢ ውስጥ |
ኪ.ግ |
32,680 |
65,000 |
ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
|
2 |
15KV 3*95+25 ABC Cable |
ጎፋ ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት |
ኪ.ግ |
156,924 |
930,000 |
ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
|
15KV 3*50+25 ABC Cable |
46,500 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡– ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲየን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ auction.et መሰረት (ለአልሙኒየም እና ለብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ) መሆኑን እየገለጽን፤ መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡
1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ ንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲየን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(Bid Security) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስም ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡
6. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር(Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
8. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ ከሚገለፅበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ከፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት የመፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለውድድር ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፡፡
9 ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ ሊደረግ ይችላል፡፡
10. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 09-05-11-55-11 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
12. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 0111-11–98-97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት