Your cart is currently empty!
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት የተለያዩ ያገለገሉ እና ያላገለገሉ የግብርና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ያገለገሉ እና ያላገለገሉ ልዩ ልዩ የግብርና
ስራ መገልገያ እቃዎች ሽያጭ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞረትና ጅሩ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ንብ/አስ/ቡድን በ2018 በጀት አመት የተለያዩ ያገለገሉ እና ያላገለገሉ የግብርና መገልገያ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት መግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ምድብ /ሎት/ መሰረት እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- ሎት አንድ – ቪቪኤም፣
- ሎት ሁለት – የተለያዩ የስንዴ፣ የጤፍ መዝሪያ እና መውቂያ ማሽኖች፣
- ሎት ሶስት – ፔዳልፓፕ፣ ሮፕ ፓፕ፣ ዘር ማሻ በርሜል፣ ፒኮ ፕሮጀክተር ሲሆኑ
1. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሰነዶችን ለእያንዳንዳቸው ምድብ/ ሎት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በሞ/ጅ/ወ/ገ/ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 115 ገንዘቡን በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከግን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
2. የእቃዎቹን አይነት እና ዝርዝር ሁኔታ ለማየት ከፈለጉ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 /ሁለት ሰዓት ተኩል/ እስከ 11፡30 /አስራ አንድ ሰዓት ተኩል/ ድረስ በሞጅ/ወ/ግ/ፑል ንብረት ክፍል በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታ ዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 /ሶስት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ/ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም በዚሁ ቀን በ3፡31 /ሶስት ሰዓት ከሰላሳ አንድ ደቂቃ/ ተዘግቶ በ4፡00 /አራት ሰዓት/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 001 ውስጥ ይከፈታል፡፡
4. የእቃው አይነት ዝርዝር መገለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች በምትጫረቱበት በእያንዳንዱ ሎት ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ለቪቪኤም 10,000 /አስር ሺህ ብር/፤ ለተለያዩ የስንዴ፣ የጤፍ መዝሪያ እና መውቂያ ማሽኖች 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/፤ ለሮፕ ፓፕ፣ ፔዳል ፓፕ እና ለዘር ማሽያ በርሜል 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ ወይም ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች በጥቅል ዋጋ ከፍተኛ የሞላ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፦ የእያንዳንዱ ሽያጭ የጨረታ መነሻ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0116 880 408 ወይም 0116 880 330 ላይ መደወል ይችላሉ፡፡
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰ/ሸዋ ዞን ገንዘብ መምሪያ የሞ/ ጀ/ ወ/ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ፋ/ ንአስ/ ቡድን