በሀዲያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪ መኪናዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና በርሜሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 24, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

በሀዲያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች መኪናዎች፣ ሞተር ሳይክሎች እና በርሜሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡-

  • ሎት – 1 መኪናዎች
  • ሎት – 2 ሞተር ሳይክሎች
  • ሎት – 3 ያገለገሉ በርሜሎች ዕቃዎች

1. ተሽከርካሪዎቹ ወይም በርሜሎች የሚገኙበት አድራሻ በሀዲያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት እና በሀዲያ ዞን የሻሾጎ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛሉ።

2. በተሽከርካሪዎች ወይም በርሜሎች ጨረታ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሳተፍ ይችላል።

3. ተጫራቾች ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና በርሜሎች ዕቃዎች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም እና የተጫራቾች መመሪያ ጋዜጣው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 15/አስራ አምስት ቀናት ውስጥ በእያንዳንዱ ተሽከርካሪ በተናጠል እና በርሜሎች በጥቅል፡ ሎት – 1 መኪና ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ፣ ሎት – 2 ሞተር ሳይክል ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ እና ሎት – 3 በርሜሎች ብር 200.00/ሁለት መቶ/ የማይመለስ ብር በመክፈል በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩትን ተሽከርካሪዎች እና በርሜሎች እቃዎች በሎት በተናጠል ወይም በድምር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመነሻ ዋጋ 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።

5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ መሙያ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15/አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታ አንድ ዋና/Original እና ቅጂ/Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻ በፖስታ ታሽጎና እንደገና ሁለቱም በአንድ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 05 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

6. ማንኛውም ተጫራች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ዋጋውን በግልጽ በአሃዝና በፊደል በመፃፍ በእያንዳንዱ በቀረበው ዋጋ ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ አለባቸው ያልተፈረመ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም።

7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሠረት ከአንድ በላይ ተሽከርካሪ ወይም ማሽነሪ መጫረት ይችላሉ።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው አስራ ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን።

9. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪዎች ወይም ያገለገሉ እቃዎች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ በተገለጸ በ10/አስር/ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ሆኖም በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ገዢው ካላነሳ ለሚደርሰው ለማንኛውም ችግር ሻጭ ተጠያቂ አይሆንም።

10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች ወይም ያገለገሉ በርሜሎች እቃዎች ከመንግስት የሚፈለግ ግብርና ቀረጥ በሻጩ የሚሸፈን ይሆናል።

11. አሽናፊው ተጫራች ተሽከርካሪዎች ወይም ያገለገሉ እቃዎች ስም ማዘዋወሪያ እና ሌሎች ልዩ ልዩ ወጪዎች በሙሉ በአሸናፊው ይሸፈናል።

12. ተጫራቾች የመነሻ ዋጋ እና የዋጋ ማቅረቢያ የጨረታ ሰነድ አካል ሲሆን ከጨረታ ሰነድ ጋር የተያያዘ ነው።

13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0923 904 503 ወይም 0910 494 153 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በሀዲያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *