መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የፕሮፔላንት ሳጥን ወይም ጋልቫናይዝድ ሺት ሜታል ስክራፕ፣ ኮፔር ክላድ ስክራፕ፤ የብረታ ብረት/ካርትሬጅ እና የብረት ችብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የፕሮፔላንት ሳጥን ወይም ጋልቫናይዝድ ሺት ሜታል ስክራፕ፣ ኮፔር ክላድ ስክራፕ፤ የብረታ ብረት/ካርትሬጅ እና የብረት ችብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 01, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1፡- የፕሮፔላንት ሳጥን ወይም ጋልቫናይዝድ ሺት ሜታል ስክራፕ፣ ኮፔር ከላድ ስክራፕ፤ የብረታ ብረት /ካርትሬጅ እና የብረት ችብስ

በመሆኑም ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን

  • ሎት 1፦ የፕሮፔላንት ሳጥን ወይም ጋልቫናይዝድ ሺት ሜታል ስክራፕ፣ ኮፔር ክላድ ስክራፕ፤ የብረታ ብረት /ካርትሬጅ እና የብረት ችብስ ሽያጩን በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለመሸጥ ስለምንፈልግ፤ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤

እንዲሁም በሰንጠረዥ የተጠቀሰዉ የአንዱ ኪ.ግ በተገለፀው ዋጋ መሰረት እንዲነገር እንገልፃለን።

1. ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የወቅቱን ግብር የከፈለ፤

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም እንደ አስፈላጊነቱ ለኤክሳይስ ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤

3. ተጫራቹ የተሰጠዉን የጨረታ ቅጽ በአግባቡ መሙላት አለበት፡፡

4. በጨረታ እንዳይሳተፍ በባለስልጣኑ ያልታገደ መሆኑን የሚገልፅ፤

5. የታክስ ክሊራንስ መቅረብ የሚችል፤

6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የማወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ሰነዱም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ15 ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዝርዝሩን ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ፡፡

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 1% በ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. ማናቸዉም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ አንድ ወጥ በሆነ በአራት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው፡- 1ኛ ቅጅ ላይ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት፤ 2ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶክመንት፤ 3ኛ ኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒ እና 4ኛ ኦርጅናል ፋይናንሻል ዶከመንት ኮፒ በማለት በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ማለትም ከ24/08/2018 ዓ.ም እስከ 08/09/2018 ዓ.ም ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡

10. ጨረታው በ09/09/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

11. የጨረታ ሰነዱ እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው አምቦ ሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ የሚገኘው ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡- የልማት ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የጨረታ ሰነዱ እና የጨረታ ሳጥኑ የሚገኘው ሆሚቾ አሙኒሽን ኢንጂነሪንግ እንዱስትሪ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0969391969 ወይም +251-11-2-19-00-42 ይደውሉ።

ተ.ቁ

የንብረት ዓይነት

መለኪያ

የአንዱ ዋጋ በብር

መግለጫ

1

የፕሮፔላንት ሳጥን ወይም ጋልቫናይዝድ ሺት ሜታል ስክራፕ

በኪ.ግ

70

 

2

ኮፔር ክላድ ስክራፕ

በኪ.ግ

55

 

3

የብረታ ብረት /ካርትሬጅ ስክራፕ

በኪ.ግ

80

 

4

የብረት ችብስ ስክራፕ

በኪ.ግ

20

 

 የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የሆሚቾ አሙኔሽን ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *