የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 12, 2026)

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡-

  • ሎት 1 የተለያዩ ብረታ ብረት
  • ሎት 2- የተለያዩ የውኃ ሞተሮች
  • ሎት 3 የተለያዩ የውኃ ፓንፖች
  • ሎት 4- የውኃ ቆጣሪዎች
  • ሎት 5 የተለያዩ ፒፒሲዎች
  • ሎት6- የተለያዩ ጂሰ ፓይፕ
  • ሎት 7- ኮምፒተሮች
  • ሎት 8- የተለያዩ የመኪና ጎማዎች

ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ያሉትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 7(ሰባት) የሥራ ቀኖች ድረስ፤

1. የድርጅቱ አድራሻ የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዝቋላ ሆቴል ወደ ድሬ አዱላላ በሚወስደው መንገድ የሽያጭ ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

2. የጨረታ ሠነዱን መግዣ ሰዓት ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ 7፡30-9፡00 ሰዓት ብቻ ነው።

3. የንብረቶቹን ሁኔታ ግልጽ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት 3፡00-11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ አርሰዲ ከሎለ በመገኘት ማየት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 7(ሰባት) ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ በድርጅቱ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችዋል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ የጨረታ ማስረከቢያ  በባንክ የተረጋገጠ CPO ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በድርጅቱ የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ስም በማዘጋጀት እና ዋጋ ማቅረቢያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ግልጽ ጨረታው ከወጣበት /07/ ሰባተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡45 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7. መ/ቤቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-430-05-17 /011-437-16-83 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይችላል።

9. የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

 የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ

የመጠጥ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት