Addis Zemen (May 12, 2026)
የብረታ ብረት ጨረታ ማስታወቂያ
ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር ብዛት ያላቸው ያገለገሉ የመስኮት መስታወት ከነፍሬሙ፤ በሮች ባለ መስታወት ከነሙሉ ፍሬማቸው፤ ተነቃቃይ ብረቶች፤ የተለያዩ መጠን ያላቸው ቶቦላሪዎች፤ ዜድ ብረቶች፣ ቲ ብረቶች እና የመስኮት መስታወቶች በአጠቃላይ ብዛት ያላቸው ሌሎች የተለያዩ ብረታ ብረት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ቁጥር ያለው፤
3. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 5፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ብሎክ 8 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአክሲዮን ማህበሩ ጽ/ቤት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ7፡30 ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
5. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዱን በታሸጋ ፖስታ በማድርግ ለዚህ በተዘገጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
6. አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
7. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፤
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ብር 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በአክሲዮን ማህበሩ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር መመለስ ይኖርበታል።
9. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት (ግለሰብ) ባሸነፈባቸው ዕቃዎች በውስጥ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በራሱ ወጪ ማንሳት ይኖርበታል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-279-3065
ታህሰብ የንግድ ስራዎች አክሲዮን ማህበር