የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተለያዩ አገልግሎት ላይ የዋሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተለያዩ አገልግሎት ላይ የዋሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 13, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

ተ.ቁ

አገልግሎት  ላይ የዋሉ የዕቃ  አይነቶች

መለኪያ

የጨረታ ማስከበሪያ በብር

1

የተለያዩ ዓይነት ፕላስቲኮች(used Plastic Rolls & Plastic Bags)

በኪሎ

200,000.00

2

አገልግሎት ላይ የዋሉ ኮምፒውተሮች (used System Unit)

በቁጥር

100,000.00

3

አገልግሎት ላይ የዋሉ የኮምፒውተር ሞኒተሮች (used Monitors)

በቁጥር

100,000.00

4

አገልግሎት ላይ የዋሉ የኮምፒውተር ኪይቦርድ(used Keyboards)

በቁጥር

100,000.00

5

የኮምፒውተር ዩፒኤስ ከነባትሪው (used UPS with batteries)

በቁጥር

100,000.00

6

የኮምፒውተር ማውዝ (used Mouse)

በቁጥር

100,000.00

7

የተለያዩ አይነት ፕሪንተሮች

በቁጥር

100,000.00

8

የተለያዩ አይነት አይአር ፕሪንተሮች (used lER thermal printer)

በቁጥር

100,000.00

9

የተለያዩ ዓይነት ኔትዎርክ ኬብሎች (used Network cables)

በኪሎ

 

50,000.00

10

የተለያዩ ዓይነት የኤሌክትሪክ ገመዶች (used power cables)

በኪሎ

 

50,000.00

11

የተቃጠለ የሞተር ዘይት (used Burned Motor Oil) (በርሜሉን ሳይጨምር))

በበርሜል

100,000.00

12

የአውሮፕላን ነዳጅ (used Defueled Oil)(በርሜሉን ሳይጨምር))

በበርሜል

100,000.00

13

አገልግሎት ላይ የዋለ ሃይድሮሊክ እና ስካይድሮል ዘይት (used Hydraulic / Sky droll Oil) (በርሜሉን ሳይጨምር))

በበርሜል

100,000.00

14

የምግብ ዘይት (used Edible Oil) (በርሜሉን ሳይጨምር))

በበርሜል

100,000.00

15

ከዉሃ ጋር የተቀላቀለ የሞተር ዘይት, የምግብ ዘይት, የሃይድሮሊክ እና ስካይድሮል ድብልቅ ውኃ (used Edible Oil, Motor Oil, Hydraulic Skydrol, Defueled Oil Mixed with Water)

በበርሜል

100,000.00

 

16

የአውሮፕላን እና የተሽከርካሪ ባትሪዎች (USED A/C & VEHICLE BATTERIES)

በቁጥር

100,000.00

17

የተለያዩ ዓይነት አሉሚኒየም ፎይሎች (used Almunium Foil)

በኪሎ

 

100,000.00

18

የተለያዩ ዓይነት የትራስ ሽፋን (used EY- Pillow Case) and አገልግሎት ላይ የዋሉ የጭንቅላት ማስደገፊያ ሽፋን (used EY headrest cover)

በኪሎ

 

100,000.00

 

19

የበረራ አስተናጋጅ ሻንጣዎች (used CABIN CREW FOLLOW-ME)

በቁጥር

100,000.00

20

የበረራ አስተናጋጅ ሻንጣዎች (used CABIN CREW LUGGAGE (SAMSONITE)

በቁጥር

100,000.00

21

የአብራሪዎች ሰነድ መያዝ ሻንጣዎች (used PILOT DOCUMENT BAGS (BRIEFCASE))

በቁጥር

100,000.00

22

የሴቶች ተንጠልጣይ ቦርሳ(used CABINCREW HANDBAG)

በቁጥር

100,000.00

 

23

የውኃ መያዣ ፕላስቲኮች (used Plastic Botteles)

በኪሎ

 

50,000.00

24

አገልግሎት ላይ የዋሉ የተለያዩ ዓይነት በርሚሎች (used Barrels)

በቁጥር

100,000.00

25

የተለያዩ 10-19 ሊትር ጄሪካኖች ክዳን ያለው እና የሌለው(used PLASTIC JERICAN 10-19 Lt.WITH & WITHOUT Lid)

በቁጥር

50,000.00

 

26

የተለያዩ ዓይነት ላፕቶፖች (used Laptop)

በቁጥር

100,000.00

27

የተለያዩ ዓይነት ታብሌቶች(used Tablet)

በቁጥር

100,000.00

28

አገልግሎት ላይ የዋሉ ፈርኒቸሮች(used Furniture)

በኪሎ

 

100,000.00

29

የተለያዩ ዓይነት ፕላስቲክ ታንከሮች ባለ(1000 Lt)(used IBC Tanker)

በቁጥር

100,000.00

ማሳሰቢያ

ሀ) በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 600.00 (ሰድስት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር WMNA/C &SAT 003/2018 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

 ለ) በማናቸውም ግዜ የጨረታ ሰነድ የዋጋ መግለጫ ላይ የሚገለፀው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታክስ እና ሌሎች ማናቸውንም አይነት አስፈላጊ ክፍያዎችን አያካትትም፤ ማናቸውንም የቫት፤ የታክስ እና ሌሎች አስፈላጊ ከፍያዎችን በሙሉ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፤

ሐ) ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኦሪጅናል (Deposit ship) በመያዝ የጨረታ ሠነዱን ግንቦት 20,2018 ዓ/ም እና ግንቦት  21,2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:30 እንዲሁም ከሰዓት 8:00 እስከ 10:00 ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት መግቢያ በር ድረስ ትኬት ቢሮ በር አጠገብ በመምጣት መግዛት ይችላሉ።

መ) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና ግንቦት 25,2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:30 እንዲሁም ከሰዓት 8:00 እስከ 10:00 ባለው ግዜ በድርጅቱ ቅጥር ግቢ በቡልቡላ በር በኩል በአካል በመገኘት መመልከት/ መጎብኘት ይችላሉ።

ሠ) ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የዕቃዎች አይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ /BID Bond/ በባንክ የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CRO) ብቻ በቅድሚያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ። ለጨረታው ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም።

ረ) ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 27,2018 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይሆናል የጨረታው አሸናፊም በዚሁ ሰዓት ተጫራቾች ባሉበት ወዲያውኑ ተለይቶ ይታወቃል። ተጫራቾች በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 4፡30 ሠነዳቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የዋና መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠገብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond) የሚገዙበትን ዋጋ ከሞሉበት የጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

ሰ) በትክክል የማይነበብ ፣ያልታሸገ ፖስታ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም። በተጨማሪም የጨረታ ማሰያዣ (CPO) የሚያስገቡት ሠነድ ውስጥ ካልተካተተ ሠነዱ ውድቅ ይደረጋል።

ሸ) ከተራ ቁጥር 11 እስከ 15 ላይ ላሉት በድርጅቱ የውስጥ አሠራር መሠረት የሽያጭ ውል የሚደረግባቸው ከሐምሌ 13, 2018 July 20,2026), ተራ ቁጥር 16 ላይ ላለው የዕቃ ዓይነት ደግሞ በድርጅቱ የውስጥ አሠራር መሠረት የሽያጭ ውል የሚደረግባቸው ሰኔ 15, 2018(June 22,2026):: እንዲሁም ከተ/ቁ 1-6 እና 17-23 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች አሸናፊ እንደተገኘ የሽያጭ ውል ከተፈጸመ በኋላ ድርጅቱ ዕቃዎቹ በሚጠራቀሙበት ጊዜ እንዲያነሱ ሲያሳውቅ ክምችቱን በ3 የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው

ከተራ ቁጥር 7-10 እና 24-29 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በሶስት (3) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ።

ቀ) ከተራ ቁጥር 1-10 እና ለተራ ቁጥር 16, 26 እና 27 ለተገለጹት የዕቃ ዓይነቶች ለሚጫረቱ ተጫራቾች በአዋጅ ቁጥር 1090/2010 መሰረት ለአደገኛ ቆሻሻዎች በዋናነት ጥቅም ላይ ለዋሉ የተለያዩ ዘይቶች፣ነዳጅ፣ናፍጣ እና ባትሪዎች እንዲሁም በደንብ ቁጥር 425/2010 ለተዘረዘሩት የኤሌክትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ቆሻሻዎች እንዲሁም ከተራ ቁጥር 11-15′ እና 17-18 በአዋጅ ቁጥር 299/1995 በደንብ ቁጥር 21-2006 መሰረት ከሚመለከተው የኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አካባቢን በማይበክል መንገድ ለመሰብሰብ፣ ለማጓጓዝ፣ መልሶ ለመጠቀም እና ለማስወገድ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ፡– ከተራ ቁጥር 1 እስከ 18 እና በተራ ቁጥር 26 እና 27 ለተዘረዘሩት እቃዎች ማነኛውም ተጫራች የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ሳያኖረው መወዳደር አይችልም በተጨማሪም ከቀበሌ፣ ከወረዳ ፣ከከተማ አስተዳደር እና ከክልል የአካባቢ ጥበቃ ቢሮዎች የተሰጡ የድጋፍ ደብዳቤዎች፣የአካባቢ እና ማህበረሰብ ተጽእኖ ግምገማ ሪፖርቶች እንዲሁም ከአዋጅ 1090/2010 እና ከደንብ 425/2010 አግባብ ውጭ የሚቀርቡ የብቃት ማረጋገጫ | ሰርተፍኬቶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

በ) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ በሚመጡበት ጊዜ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች።

1. የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (2018 ዓ/ም) (ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይቶች)።

2. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 እንዲሁም ከተ/ቁ 11 እስከ 17 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሠርተፊኬት ሠነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ሠነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል።

3. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 18 እና ለተ/ቁ 23, 26 እና 27 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች የአካባቢ ጥበቃ ሴርተፊኬት ሠነዱን በሚያስገቡበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ካልሆነ ሠነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል።

4. ማንነታቸውን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፤ፓስፖርት ወይንም የታደሰ መንጃፈቃድ ማምጣት ይኖርባቸዋል። (ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይነቶች):: የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን የጨረታ ሠነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህን ለማያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሠነድ የማንሸጥ መሆናችንን እንገልጻለን።

ተ) ተጫራቹ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት በሚሆንበት በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበው የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ መሆኑን የሚያስረዳ ሰነድ (በሚመለከተው አካል የተመዘገበና የጸደቀ የመመስረቻ ፅሁፍ እና/ወይም ቃለ ጉባኤ)  እና የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።

ቸ) የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በጨረታ ማስታወቂያው ወይም በውሉ በተቀመጠው የግዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባይወስድ/ባያነሳ፤ ክፍያ ባይፈጽም፣ (ውል በሚያስፈልግበት ግዜ ውል ለመፈጸም ፈቃደኛ ባይሆን) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ወዲያውኑ ይሰረዛል፤ እንዲሁም ጨረታው በድጋሚ በሚወጣበት ወቅት የዋጋ ልዩነት ከመጣ ልዩነቱን እንዲከፍል ይገደዳል፤

ኀ) ማንኛውም አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚያነሳበት ጊዜ ዕቃዎቹን መምረጥ አይችልም።

ነ) ከተራ ቁጥር 1 እስከ 18 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች አሸናፊወች አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመስክ ምልከታ(Facility Visit)እንደሚደረግ እና መስፈርቱን እማያሟሉ ከሆነ የሽያጭ ውል የማይፈፀም መሆኑን እናሳውቃለን። እንዲሁም ከተ/ቁ 17 እስከ 18 ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ቆራርጦ እና ፈጭቶ መጠቀሙን ማሳየት የሚችል መሆን አለበት።

ኘ) ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ግዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አ) ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የተረከቡትን ማነኛውንም ያገለገሉ እቃዎች በተሻለ አካባቢያዊ፣ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በሚሰጥ መልኩ የሚያስወግዱ፣ ጥቅም ላይ የሚያውሉ እና የላቀ አቅም ያላቸው ህጋዊ ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ። ይህም ተፈጻሚ የሚሆነው የጸደቀ የአካባቢ እና ማህበረሰብ ተጽእኖ የጥናት ሪፖርት እና ተከታታይ የአፈጻጸም የኦዲት ሪፖርት ያቀረቡ፣ በአለም አቀፍ የጥራት እና የአካባቢ አያያዝ ስታንዳርዶች ተገቢ እውቅና ያላቸው እና ያቀረቡ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የስራ ሁኔታን ከግምት በማስገባት የሚመጣጠን አገልግሎት በውሉ መሰረት ለመስጠት አቅም ያላቸው መሆኑን የሚያስረዱ ሰነዶች ለምሳሌ የጭነት አገልግሎት መኪኖች ባለቤትነት፣ በቂ የሰው ሃይል(በዉል የተደገፈ)፣ የተደራጀ የአሰራር ዘዴ(ፖሊሲ፣ ማኑዋል፣ መመሪያ)፣ በቂ ማሽነሪ እና የስራ ቦታ ይዞታ ሰነዶች ወይም ማስረጃዎችን ማቅረብ ሲችሉ ብቻ ነው።

ለበለጠ መረጃ እና ሰነድ ለመግዛት እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ-ሥልክ ቁጥሮች + 251-11 517-8824

+251-11 517-8781