የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም ብረታ ብረቶች፣ ለማገዶ የሚሆን እንጨት፣ የበረንዳ ቋሚ ጣውላ፣ ወረቀት፣ ጎማ ባለ ሽቦ እና ጎማ ሽቦ የሌለው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 04, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 2018 በጀት ዓመት ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም ብረታ ብረቶች፣ ለማገዶ የሚሆን እንጨት፣ የበረንዳ ቋሚ ጣውላ፣ ወረቀት፣ ጎማ ባለ ሽቦ እና ጎማ ሽቦ የሌለው በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡

1. የጨረታ ሠነዱን ከወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ 2 ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከግ//አስ/ ዳ/ሬት 50 ብር በመክፈል መውሰድ ይቻላል።

2. ሽያጩ የሚከናወነው በወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ግቢ በሚገኘው በአስተዳደር /ቤት አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል።

3. ንብረቶቹን ማየት የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሠነዱን ከገዛ በኋላ ወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ግቢ ውስጥ ያለውን ንብረት ከሰኞ እስከ አርብ ድረስ በስራ ሰዓት ቀርቦ ማየት ይችላል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ

  • ለብረት/ስቲል ብር 5,000 /አምስት ሺህ/
  • ለማገዶ እንጨት ብር 5,000 /አምስት ሺህ/
  • የበረንዳ ቋሚ ጣውላ ብር 2,500 /ሁለት ሺህ አምስት መቶ/
  • ለወረቀት ብር 10,000 /አስር ሺህ/
  • ለጎማ ብር 5000 /አምስት ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ .. ማስያዝ ይችላሉ።

6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች ንብረቱን በሁለት ቀን ውስጥ ሙሉ ክፍያውን ከፍሎ ማንሳት አለበት። ንብረቱን በተጠቀሰው ቀን ካላነሳ ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

7. /ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡ስልክ ቁጥር 046 551 2116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ወላይታ ሶዶ