የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 26, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 003/2025/26

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ንቃይ የእንጨት በሮችና የእንጨት ወንበሮች፣ንቃይ ቴለር ካውንተርና የእንጨት ፓልቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ንብረቶች፣ የተለያዩ ብረታ ብረቶች እና የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖችና ከተሽከርካሪ የተፈቱ ብረታ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡ 00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 02 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።

3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።

4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።

5. ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።

6. ተጫራች ለሚጫረትበት ያገለገሉ ንብረቶች የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) ወይም ለምድቡ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለኢትየጵያ ንግድ ባንክ ያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) ሲ.ፒ.ኦ. ተዘጋጅቶ ማስያዝ ይኖርበታል።

7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው