የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Apr 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን —

  • ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች
  • ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት
  • የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

ማንኛውም የስም ማዛወሪያ ተጨማሪ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር፣ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ክፍሎ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ከሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /Ethiopian Insurance corporation/ ስም በተሰራ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት ይችላል።

ሀ/ የዕቃ ማስያዣ – የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው።

ለ/ የተሸከርካሪ ማስያዣ

የጨረታ መነሻ

እስከ ብር 50,000.00

20 በመቶ

ከብር 50,001.00

እስከ ብር 100,000.00

ብር 15,000.00

ከብር 100,001.00

እስከ 200,000.00

ብር 25,000.00

ከብር 200,001.00

እስከ 300,000.00

ብር 37,000.00

ከብር 300,001.00

እስከ 400,000.00

ብር 50,000.00

ከብር 400,001.00

እስከ 500,000.00

ብር 60,000.00

ከብር 500,001.00

እስከ 800,000.00

ብር 75,000.00

ከብር 800,001.00

ብር በላይ

ብር 100,000.00

 ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ግንቦት 10 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ግንቦት 11 ቀን 2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ተራቾች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150 ( አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይከፍላሉ።

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 439-2589 እና 011 439-2545 መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *