Melekite Dire (Apr 22, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የድሬዳዋ አ/አቀፍ ኤርፖርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
ለጨረታ የቀረበ የአንዱ ዋጋ ከቫት በፊት |
|
1 |
የብረት ፖውዛ ፖል (Steel Pole) 20ሜትር |
በኪሎ |
100,0000
|
|
|
2 |
ስብርባሪ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት |
በኪሎ |
200,000 |
|
|
3 |
ስብርባሪ ቁርጥራጭ አልሙኒየም |
በኪሎ |
100,0000 |
|
|
4 |
ስብርባሪ ቁርጥራጭ ፕላስቲክ |
በኪሎ |
50,000 |
|
|
5 |
የውሃ ፖምፕ 20 የፈረስ ጉልበት |
በቁጥር |
100,0000 |
|
ማሳሰቢያ
ሀ) በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ለመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የጨረታ ቁጥር DA/DIR 001/2018 በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
ለ) በማናቸውም ግዜ የጨረታ ሰነድ የዋጋ መግለጫ ላይ የሚገለፀው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የታክስ እና ሌሎች ማናቸውንም አይነት አስፈላጊ ክፍያዎችን አያካትትም፤ ማናቸውንም የቫት፤ የታክስ እና ሌሎች አስፈላጊ ክፍያዎችን በሙሉ የጨረታው አሸናፊ ይከፍላል፤
ሐ) ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኦሪጅናል (Deposit slip) በመያዝ የጨረታ ሠነዱን ከሚያዝያ 26-28, 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 08:00 እስከ 10:30 ድሬዳዋ አ/አቀፍ ኤርፖርት አስተዳደር ቢሮ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ ፣ በአካል ተገኝተው ጨረታውን መግዛት ለማይችሉ በተራ ቁጥር ሀ በተጠቀሰው መሰረት ግቢ የተደረገበትን ደረሰኝ እና የተጠቀሱትን ሰነዶች በማያያዝ በኢ-ሜይል ShimelisG@ethiopianairlines.com በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግፕት ይችላሉ።
መ) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና ሚያዝያ 29-30 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 08:00 እስከ 10:30 ባለው ግዜ ውስጥ በድሬዳዋ አ/አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት መመልከት/መጎብኘት ይችላሉ።
ሠ) ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የዕቃዎች አይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ /BID Bond/ በባንክ የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ብቻ በቅድሚያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ ለጨረታው ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም፡፡
ረ) ተጫራቾች በድሬዳዋ አ/አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ግንቦት 3,2018 ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት 08:00 እስከ 10:30 ሠነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ለሚወዳደሩበት የዕቃ ዓይነት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond) የሚገዙበትን ዋጋ ከሞሉበት የጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
ሰ) ጨረታው የሚከፈተው ግንቦት 5 2018 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋናው መስሪያ ቤት ይሆናል። የጨረታው አሸናፊም በደብዳቤ ይገለፃል። አጠቃላይ የጨረታው ውጤት በድሬዳዋ አ/አቀፍ ኤርፖርት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚለጠፍ ይሆናል።
ሽ) በትክክል የማይነበብ ፣ያልታሸገ ፖስታ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው ሠነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በተጨማሪም የጨረታ ማሰያዣ (CPO) የሚያስገቡት ሠነድ ውስጥ ካልተካተተ ሠነዱ ውድቅ ይደረጋል።
ቀ) ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በሶስት (3) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ግቢ በማድረግ እቃዉን የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ::
በ) ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሊገዙ በሚመጡበት ጊዜ ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች
1.የታደሠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (2018 ዓ/ም)(ለተዘረዘሩት ሁሉም የዕቃ ዓይቶች)፡፡
2. ማንነታቸውን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ፤ፓስፖርት ወይንም የታደሰ መንጃፈቃድ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን የጨረታ ሠነድ በሚገዙበት ጊዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህን ለማያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሠነድ የማንሽጥ መሆናችንን እንገልጻለን።
ተ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ሰነዱን በሚያስገቡበት ግዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ይደረጋል።
የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን የጨረታ ሰነዱን በሚገዙበት ግዜ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ። ይህንን ለማያሟላ ማንኛውም ተጫራች ሰነዱ የማንሸጥ መሆናችንን እንገልፃለን።
ቸ) የተጫራቹ ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በጨረታው ለመሳተፍ የቀረበው የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ (ህጋዊ ተወካይ) መሆኑ የሚያስረዳ ሰነድ ፣ በሚመለከተው አካል የተመዘገበ እና የፀደቃ መመስረቻ ፅሁፍ ፣ ቃለ-ጉባዩ እና የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።
ኀ) የጨረታው አሸናፊ ባቀረበው ዋጋ መሰረት በጨረታ ማስታወቂያው ወይም በውሉ በተቀመጠው የግዜ ገደብ ውስጥ እቃውን ባይወስድ/ባያነሳ፤ ክፍያ ባይፈጽም፣(ውል በሚያስፈልግበት ግዜ ውል ለመፈጸም ፈቃደኛ ባይሆን) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ወዲያውኑ ይሰረዛል፤ እንዲሁም ጨረታው በድጋሚ በሚወጣበት ወቅት የዋጋ ልዩነት ከመጣ ልዩነቱን እንዲከፍል ይገደዳል፤
ነ) ማንኛውም አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚያነሳበት ጊዜ ዕቃዎቹን መምረጥ አይችልም፡፡
ኘ) በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘበ (Bid Bond) በሚቀጥሉት ሁለት (5) የሥራ ቀናት ተመላሽ ይሆናል።
አ)ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ እና ሰነድ ለመግዛት እነዚህን ሰልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ
ሥልክ ቁጥሮች +259-04-05-20-87/ +2519-11-00-50-05