Be'kur (May 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጎጃም አስ/ዞን የእነማይ /ወ/ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ቡድን በእነ/ወ/ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ከየንብረት ክፍሎች የተሰበሰቡ የሚወገዱ የተለያዩ አሮጌ ብረታ ብረቶች በሽያጭ ለማስወገድ በአንድ ቦታ ላይ ተሰብስበው ስለሚገኙ የጽ/ቤታችን አጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አሮጌ ብርታ ብረቶች እንዲሸጡ ጽ/ቤቱ ባዘዘን መሰረት በግልጽ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል ፤
የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. የምትገዙበትን ዋጋ ግልፅ በማድረግ በመፃፍ፣ ፊርማና ስም በማስቀመጥ፣ በፖስታ በማድረግ እነማይ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳድር ቡድን ቢሮ ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችኋል።
2. ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
3. መ/ቤቱ ካቀረበው መነሻ ዋጋ በታች የቀረበ የመወዳደሪያ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
4. አሸናፊው ያሸነፋቸውን አሮጌ ብርታ ብረቶች በ10 የስራ ቀናት ውስጥ በራሱ ማንኛውንም ወጭ በመሸፈን መውሰድ አለበት።
5. የጨረታ ማቅረቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚውል ሲሆን በ16ተኛው ቀን 3፡30 ይታሽጋል።
6. ጨረታው የሚከፈተው በእለቱ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ባይገኙ ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡ የሚከፈትበት ቀን እሁድ፣ ቅዳሜ እና በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን የመክፈት ሂደት ለሚተላለፍ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ 20‚000 (ሃያ ሽህ) ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጫረታ ሰነድ የማይመለስ 300(ሶስት መቶ ብር) ፋይናንስ ቡድን ከገ/ያዥ መግዛት አለባችሁ።
9. ተጫራቾች ባንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መሙላት አይቻልም፤ በተጨማሪ አንደኛው ተጫራች አሸንፎ አልወስድም ቢል የጨረታ ማስከበሪያው ተወርሶ ሁለተኛው ተጫራች በአንደኛው ባሸነፈበት ዋጋ መውሰድ ይችላል።
10. ተጫራቾች ዋጋ ለመሙላት ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሲሆን፡፡ የጨረታ ሰነዱን እነ/ወ/ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ላይ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
11. በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ አሻሚ ነገሮች መኖር የለባቸውም፡፡ስርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት።
12. አሸናፊው የሚለየው በአንድ ኪሎ ግራም ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበው ነው።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የእነማይ ወ/ገ/አ/ል/ጽ/ቤት