Addis Zemen (Jun 28, 2026)
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ፋብሪካችን የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ የብረት ተረፈ ምርቶችን በጥሬ ዕቃነት ለብረት ማቅለጫ ፋብሪካዎች ወይም ለሌላ ግልጋሎት ሊያገለግሉ የሚችሉትን የብረታ ብረት ተረፈ–ምርቶችን፤ Painting Cane, Carton, Welding Electrode Tips, Old Griding Disks በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች/ ግለሰቦች ማሰረጃቸውን በመያዝ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 በብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ብትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንጻ 4ኛ ወለል በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ ተረፈ–ብረቶቹን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን ጥሬ ዕቃ የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል፡፡
ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፣ 251-552 2681 / 251-552 2731
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ