መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ የተቃጠለ ዘይትና ጀሪካን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ አ.ማ. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ የተቃጠለ ዘይትና ጀሪካን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Jun 28, 2026)

ያገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ

አክስዮን ማህበራችን መድን ፋና ትራንስፖርት ሎጂስቲክስና ንግድ . የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፣ ጎማዎች፣ የተቃጠለ ዘይትና ጀሪካን በጨረታ በማወዳደር ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ መሸጥ ይፈልጋል

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል::

1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 22 ቀን 2018 . ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ዋናው መስሪያ ቤት በሚገኝበት ጎተራ ማሳለጫ ከአቦኝ ህንጻ አጠገብ በመገኘት ከቢሮ ቁጥር 13 የማይመለስ ብር ሦስት መቶ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::

2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሰረት ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) እስከ ብር 10,000 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአክስዮን ማህበሩ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውንና የሚወዳደሩበትን ሎት በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤምቨሎፕ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል::

4. ጨረታው መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 29 ቀን 2018 . 800 ላይ ታሽጎ በእለቱ 830 ላይ ይከፈታል::

ማሳሰቢያ፡

  • ተጫራቾች ዕቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በአካል ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
  • አክስዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ

በመደበኛ ስልክ ቁጥር: 0114708186

በተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር: 0913-300714 መደወል ይችላሉ