በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እስክራፕ ብረቶችን፣ ካስቶችን እና አልሙኒየሞችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ እስክራፕ ብረቶችን፣ ካስቶችን እና አልሙኒየሞችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ሰነድ ቁጥር ቢ.ሞ.ቬ.ኢ.ኢ./ግጨሰ/01/2018

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ  ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን ከታች በዝርዝር የቀረቡትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. እስክራፕ ብረቶችን
  2. እስክራፕ ካስቶችን
  3. እስክራፕ አልሙኒየሞችን

በዚህም መሰረት ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ማንኛውም ተጫራች አግባብነት ያለው በዘርፉ በ2013 ዓም የታደሰ ንግድ  ፈቃድ ያላቸውና የወቅቱን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ (VAT) የተመዘገቡና (Tin No) ያላቸው መሆን አለበት።
  3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለፅና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የሚገዙበትን የአንድ ኪሎ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።
  5. በጨረታ እንዳይሳተፉ በባለስልጣኑ ያልታገደ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  6. የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
  7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በማያሻማ ሁኔታ መግለጽና ሙሉ አድራሻቸውን መጥቀስ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመጫረቻውን ጠቅላላ ዋጋ 2% (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ 2% (CPO) ያላስያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል።
  9. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች 2% የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ዋስትና የጨረታ አሸናፊው እንደታወቀ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
  10. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፤ ለወደፊትም በኢንዱስትሪው ጨረታ አይሳተፉም ያስያዙትም የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል።
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራች ከኢንዱስትሪው ጋር የሥራ አፈፃፀም ውል መፈራረም አለበት ውል ካልፈረመ ያስያዘው 2% (CPO) ተወርሶ ለኢንዱስትሪው ገቢ ይደረጋል።
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በግልፅ በኢትዮጵያ ብር ነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር መስፈር አለባቸው። በዋጋው ላይ ማንኛውም ታክስና ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ መሆኑና አለመሆኑ መገለፅ አለበት።
  13. በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር ነጠላ ዋጋ ተቀባይነት እንዲኖረው ተደርጎ በነጠላ ዋጋው ተመስርቶ ጠቅላላ ዋጋው ይታረማል።
  14. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ሳጥኑ ከሚዘጋበት ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  15. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በሁለት ቅጅዎች ማቅረብ አለባቸው አንደኛው ቅጅ ላይ “ዋና” በሁለተኛው ቅጅ ላይ “ኮፒ” የሚል ምልክት ማድረግ ይኖርባቸዋል። በሁለቱ መካከል ያለመጣጣም ቢፈጠር “ዋና” ተብሎ ምልክት የተደረገበት ተቀባይነት ይኖረዋል።
  16. ማንኛውም ተጫራቾች በሚቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ወይም የሕጋዊ ወኪሉ ስም ፊርማና የድርጅቱ ማህተም መስፈር አለበት።
  17. በሌላ ተጫራች ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  18. ከዚህ በላይ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በግንባር ቀርበው ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር ) በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፤
  19. ጨረታው ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይበት ጊዜ የግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የመንግስት የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የስራ መውጫ ባሉት ሰዓቶች ሲሆን ጨረታው በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያኑ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በገዙበት ተቋም በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። እንዲሁም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
  20. ኢንዱስትሪው ያወጣውን ጨረታ ሰነድ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድሩ ውጪ ይደረጋል።
  21. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈራረሙ የውል ማስከበሪያዋስትና (Performance Bond) ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% (አስር ከመቶ) በተመሰከረለት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ውል ከተፈራረሙ በኃላ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወዲያውኑ ይለቀቅላቸዋል፤
  22. ማንኛውም አሸናፊ ንብረቱን ለማጓጓዝ የራሱን ትራንስፖርት እና የጉልበት ሰራተኛ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  23. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ማግኘት ይችላሉ።
  24. ኢንዱስትሪው ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  25. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ ቁጥር (09 94 52 15 56/ 09 11 71 25 21) ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስሪ ግሩፕ

የቢሾፍቱ ሞተር ቬይክልስ ኢነጂነሪንግ ኢንዱስትሪ

ቢሾፍቱ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *