በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 200 ቶን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 200 ቶን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 30, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ

የሽያጭ ጨረታ ቁጥር-አሽጨ 001/ኦኩስፋ/ቁ-2/2018

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሰውን ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  • ሎት 1 – ከግንባታ የተራረፉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት 200 ቶን ሽያጭ ጨረታ

ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ የተሰማራችሁና በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  2. በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ) ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30 – 6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሽገ ኤምቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 /አንድ መቶ ሽህ/ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራች ለተጫረተው ዕቃ መነሻ ዋጋ መሰረት ለመግዛት በቂ አቅም መኖሩን ለማረጋገጥ የባንክ ስቴትመንት ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  6. ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።
  7. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።
  8. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታው ዋጋ ጸንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተከታታይ 60 ቀናት ነው።
  9.  የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው።
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የጨረታው ሰነድ የሚሽጥበት የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ይሆናል።

አድራሻ፡- ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አዲስ አበባ ነው።

ለበለጠ መረጃ ይህን የስልክ ቁጥር መጠቀም ይቻላል 09 91 14 94 85 / 09 40 20 94 64

የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *