Addis Zemen (Aug 11, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በምስራቅ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ስለሚፈልግ ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በብር 200 በመግዛት እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
- ሎት 1- ያገለገሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች
- ሎት 2- ያገለገሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት 3 ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች
- ሎት 4 ከሥርዓተ ትምህርት ውጪ የሆኑ መጽሐፍቶች
- ሎት 5 ያገለገሉ ካዝናዎች ትንሹና ትልቁ
- ሎት 6 ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች
- ሎት 7-የፕላስቲክ ውጤቶች
ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች የጨረታ ሰነድ በመግዛት ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ዋጋውን በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ በሲፒኦ /CPO/ የዋጋውን 2% (ሁለት በመቶ) በማስያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 15 ተከታታይ ቀናት በአካል በመቅረብ መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የሞላውን ዋጋ በማስገባት እና የመወዳደሪያ ሰነዶችን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16 ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ደቂቃ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ቀን የእረፍት ቀን ወይም የባህል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታው ሂደት አያስተጋጉልም።
ማሳሰቢያ
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙለ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913392239 ወይም 0952179 239 በመደወል ማረጋገጥ ይቻላል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በምስራቅ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት