የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የተለያዩ ንብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 20, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ መድን ድርጅት ስም ተመዝግበው ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው እና ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ የተረከባቸውን፡- ተሽከርካሪዎችን እና የኢትዮዽያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን

  • ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች
  • ልዩ ልዩ ጋቢናዎች በተናጠል
  • ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት
  • የተለያዩ ብረታ ብረቶችን የኤሌክትሪክ ፖሎች፡ የመንገድ አጥሮች
  • የ132KV underground cables በብረት ድረም የተጠቀለሉ (6) ስድስት ጥቅሎች ባለበት
  • በኢትዮዽያ መድን ድርጅት ስም ተመዝግበው ድርጅቱ ሲጠቀምባቸው እና ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

ማንኛውም የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች ሁሉ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018ዓም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /Ethiopian Insurance Corporation/ ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ ሕጋዊ ፈቃድ ከተሰጣቸው ንግድ ባንኮች በማስያዝ መጫረት ይችላል።

ሀ/ ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ) በመክፈል ከሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል እና ለገሐር ከሚገኘው የዋና መሥሪያ ቤት ሂሳብ ክፍል ከነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓም እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2018ዓ.ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት መግዛት ይኖርባቸዋል

ለ/ የዕቃ እና የተናጠል ጋቢና ማስያዣ፡- የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው።

ሐ/ የተሽከርካሪ ማስያዣ

የጨረታ መነሻ

እስከ ብር 50,000.00

20 በመቶ

ከብር 50,001.00

እስከ ብር 100,000.00

ብር 15,000.00

ከብር 100,001.00

እስከ ብር 200,000.00

ብር 25,000.00

ከብር 200,001.00

እስከ ብር 300,000.00

ብር 37,000.00

ከብር 300,001.00

እስከ ብር 400,000.00

ብር 50,000.00

ከብር 400,001.00

እስከ ብር 500,000.00

ብር 60,000.00

እስከ ብር 500,001.00

ከብር 800,000.00

ብር 75,000.00

ከብር 800,001.00 ብር በላይ

ብር 100,000.00

  • ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት አስቀድመው በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላትና ዋናውን ሲፒኦ ከቅጂውን ሲፒኦ ጋር አንድ ላይ በኢንቨሎፕ በማሸግ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሐር በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ  ማዕከል ይከፈታል።
  • በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኃላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በጨረታ ዝርዝር ሰነድ ላይ በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 3,000.00 (ሦስት ሺህ ብር) ይከፍላሉ።
  • ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት ነው። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ
  • ማሳሰቢያ፡- አንድ የጨረታ ሰነድ ለአንድ ተሽከርካሪ ወይም በአንድ ጊዜ ለሚጫረት ንብረት ብቻ
  • የሚያገለግል ሲሆን ከአንድ በላይ መጫረት የሚፈልግ አካል በፍላጎቱ ልክ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርበታል።

ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር  011 439-2589 እና  011 439-2545 መጠየቅ ይቻላል

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *