የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ ይዞታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ ይዞታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 14, 2026)

የተወጋጅ ንብረት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- ግጨ 001/2019

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ ይዞታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት ተጫራቾች፡-

  • የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይመለያቁጥር ቲንሠርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው ዝርዝሩን ከሰነዱ መመልከት የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ፡-
  • ሎት 1. ልዩ ልዩ የፈርኒቸር ምርቶች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር)
  • ሎት 2. የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች (ሲስተም ዩኒት፣ ሞኒተር እና የተለያዩ ፕሪንተሮች) የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 (አምስት ሺ ብር)
  • ሎት 3. ቁርጥራጭ ብረታ ብረት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 (ሃያአምስት ሺ ብር)
  • ሎት 4. የብረት በርሜል፣ የዕቃ ማጠቢያ ሲንከ፣ የብረት ባልዲ፣ የብረት ካዝና፣ የቡና መፈልፈያ ቋት፣ የእሳት ማጥፊያ ሲሊንደር የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺ ብር)
  • ሎት 5. የተነጣጠሉ ዴከሰን ሼልፍ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺ ብር)
  • ሎት 6. የሣይንስ ትምህርት መርጃ አላቂና ጥሬ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሃምሳ ሺ ብር)
  • ሎት 7. የታይፕራይተር መለዋወጫ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000(አስራ አምስት ሺ ብር)
  • ሎት 8. የህትመት ተረፈ ምርቶች
    • ምድብ 1 ቁርጥራጭ ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሃምሳ ሺ ብር)
    • ምድብ 2 ሲግኒቸር ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሃምሳ ሺ ብር)
    • ምድብ 3 ኮር ያለ ወረቀት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አሥር ሺ ብር)
    • ምድብ 4 ያገለገለ ፕሌት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሃምሳ ሺ ብር)
    • ምድብ 5 ያገለገለ ፊልም የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አሥር ሺ ብር)
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ንብረቶቹ በሚገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ይከፈታል። ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ዝግ ላይ ከዋለ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  • ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቶ የተጠበቀ ነው።

የድርጅቱ ዋና መ/ቤት አድራሻ አ/አ ቦሌ ክፍለ ከተማ ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንፃ ወደ ቀኝ በILRI/ እና FOR ድርጅቶች መካከል በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ፡- በሥራ ሰዓት በ 0911758804 ወይም በ 0911866167 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የትምህርት መሣሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት