የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 28, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 033/2019

የኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር ዝርዝራቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በዝግ ጨረታ መሠረት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጠናቀቁ የጨርቅ እና ክር ተረፈ ምርቶች
  2. የተለያዩ አይነት የጥጥ ቅሪቶችና ተረፈ ምርቶች
  3. የተለያዩ አይነት ብረታ ብረት እና መለዋወጫ ዕቃዎች
  4.  የተለያዩ መጠን ያላቸው የተጋቡ የፕላስቲክ ጀሪካኖችና የብረት በርሜሎች እንዲሁም ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች

በጨረታው ማንኛውም በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት መሣተፍ የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከአክሲዮን ማህበሩ ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ ወይም ከዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ መግዛት ይችላሉ።

ዕቃዎቹን ዘወትር በስራ ሰአት ( ከሰኞ – አርብ ከ 2፡00 እስከ 10፡00 እና ቅዳሜ ከ2፡00- 6፡00) ዋናው መ/ቤት ኮምቦልቻ በመመልከት የሚገዙበትን ነጠላ ዋጋ ማህበሩ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በትክክል በመሙላት በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጨረታ መመሪያው ላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በ (CPO) በማስያዝ ከላይ በተገለጹት ቦታዎች ላይ በመገኘት ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ጨረታው ማስታወቂያው በተዘጋ በ3ኛው ቀን ኮምቦልቻ /ወሎ/ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።

አ/ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ

ስልክ ቁጥር 033-551 0627/ 551 0211(ኮምቦልቻ)

ስልክ ቁጥር 011-551 1805/ 553 0124 (አዲስ አበባ)

ራስ ደስታ ዳምጠው ጎዳና ፓፓሲናስ ህንጻ 1ኛ ፎቅ

ኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ አክሲዮን ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *