Addis Zemen (Oct 25, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 03/2019
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዘጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 03/2019 በ21/02/2019
- የተለያዩ አልባሳት፣
- ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- ጫማዎች የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣
- የሞባይል ግላሶችና ከቨሮች ፣
- የእጅ ሰዓቶች ፣
- ስፔርፓርቶች፣
- የእይታ ዕቃዎች መነፅሮች፣
- የመሬት ምንጣፍ፣
- ኮስሞቲክ እና መዋቢያዎች፣
- የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣
- የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣
- የጽሕፈት መሣሪያዎች፤
- የእስፖርት መሥሪያ መሣሪያዎች ፣
- ኳስ፣
- የተለያዩ አርትፊሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች
- የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥርን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠቅበታል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።
- በሐራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ውድአነድ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል አነድ ለመግዛት ዘወትር በሥራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ እንዲሁም ቅዳሜ ከ2 ሰዓት እስከ ቀኑ 6 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን ዕቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።
- ለሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት ዕቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
- ተጫራች በሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ ብር ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም “ ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- በሐራጅ ጨረታ ለመጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) ሰኮዱ የተቀመጠ ብር በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- የሐራጅ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያው መሰረት በዕለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን በተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደሩበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ሰባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል፣
- የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 ( 09 12 88 57 46)
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ
ቅ/ጽ/ቤት