በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 03, 2026)

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሐራጅ ጨረታ

ማስታወቂያ ቁጥር ሐ-22/2019 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 3 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ–ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/202 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶች ማለትም

  • AC ADAPTOR, 
  • HD TV CABLE,
  • TV WALL MOUNT,
  • LED HIGHBAY LIGHT, 
  • SKMEI IRON ADULT HAND WATCH,
  • WOODEN DOOR FRAME & WATER PURIFIER,
  • OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND,
  • LED STRING LIGHTS, RUBBER NAIL FILTER,
  • S/S MANICURE, METAL DECORATIVE & EYE LASH,ADULT FABRIC CAP,
  • SHOPPING BAG & OTHERS, WALL TRANSFORMER,CHEMICAL MIXING TANK, 
  • CHANNEL STEEL,
  • GALVANISED STEEL PIPE,
  • HEALD FRAME,
  • FABRIC MICRO FIBER CLEANING TOWEL,
  • SINGLE,DOUBLE PORT FACE PLATE &
  • OTHER, SCHOOL BAG, FABRIC ADULT CAP & SUPERMARKET SHELF,
  • CHIL DRED SPORT SHOES BRAND &
  • LADYSPORT SHOES BRAND,
  • CONNECTING ROD,
  • BLADE FUSE,
  • VIBRATION ANALYSIS OF CENTERFUGAL BLOWER FAN, ELECTRIC CRANE SCALE,
  • HAIR CLIPER, PERFUME &
  • TROUSER, DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER WITHOUT REFROGIRETOR፣
  •  የስቴሽነሪና ማስታወቂያ እቃዎች እና
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

  1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከአከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሸን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሽጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተስብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
  4. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ በኦንላይን የአክሸን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች በወረቀት የሚያስይዙ ከሆነ የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHOPAN CUSTOMS COMMISSION MODJO  BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
  6. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ስዓት ጀምሮ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
  8. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ አራሱን ከጨረታው ውድድር ማማለል አይቻልም፤ የስጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  9. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  10. በተራ ቁጥር 07 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንዴሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሸያጭ ይወገዳል፡፡
  11. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
  12.  ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-5511/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ወይም 022-236-01-90 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን  የሞጆ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት