የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል


Be'kur (Nov 02, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2019

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ያገለገሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን

  • ሎት 01. የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣
  • ሎት 02 የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን እና
  • ሎት 03 ጎማና ባትሪ በጠቅላላ ድምር በሎቱ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ማንኛዉም የታደሰ ብሄራዊ መታወቂያ ያለዉ ግለሰብ ወይም ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለዉ ድርጅት ሊሳተፍ ይችላል፡፡
  2. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና የሚሸጡ ንብረቶችን ዝርዝር የሚገልፅ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ለእያንዳንድዱ ዝርዝር ሰነድ በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በአማራ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው 2 በመቶ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ከፈለጉ ማስረጃውን ወይም የገቢ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከፋይናንስ (ዋጋ ማቅረቢያ) ጨረታ ሰነድ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማችን በማሰፈርና ፖስታውን በሚገባ በማሸግ የአማራ ፖሊስ ዋናዉ መስሪያ ቤት ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 06 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ገቢ በማድርግ በእለቱ 11፡30 ላይ ይዘጋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚሸጡትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን በተቋሙ እስቶር በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ዘወትር በስራ ስአት ከሰኞ አስከ አርብ ማየትና መገምገም ይችላሉ፡፡
  8. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ አሸናፊነቱ ከተገለፀት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ያሸነፋቸዉን እቃዎች ማንሳት ይኖርበታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  • ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 09 77 13 56 78 ባህርዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት

ባህር ዳር