Addis Zemen (Nov 04, 2026)
የተለያዩ ንብረቶች ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የቀለም ሮሎዎች የኤጋ ቆርቆሮ፣ የተለያዩ ወረቀቶች ፕሌቶች እና የመሳሰሉ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ላይ በፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
ስልክ ቁጥር፡- 01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ፡- 0115 51 86 96
ፖ.ሳ.ቁጥር:- 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር