Addis Zemen (Nov 13, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማኃላ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- የብረት ሞልዶች
- የብረት ኮንቴነሮች
- ራድያል ሽቦዎች
- ስኮርች ኮምፓወንድ
- የብረት፣ የፕላስቲክ እና የእንጨት ፓሌቶች
- የተለያየ መጠን ያላቸው ብላደሮች
- ያገለገሉ መካኒካል ማሽን ስፔርፓርቶች
- አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ፍላፖች
- አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጎማ የውስጥ ላስቲኮች ከመነዳሪ )
- የተጋቡ የብረት በርሜሎች
- ያገለገሉ እና አዳዲስ የውጪ ብራንድ ጎማዎች
- በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ያገለገሉ የተለያዩ የማሽን ዘይቶች
- ብረታብረቶች
- እና ሉሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች
በመሆኑም ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፤ ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ህዳር 26 ቀን 2019 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሳሪስ በሚገኘው በዋናው ሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው ህዳር 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
4. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦ ንብረት አስተዳደር መምሪይ ቢሮ
ስልክ ቁጥር፦ 011 442 15 55/234 ወይም 251974024142 መጠየቅ ይቻላል።
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር