Addis Zemen (Nov 16, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት:-
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ ለመግዛት፤
- የተለያዩ ያገለገሉ አሮጌ እቃዎች፣ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህክምና ዕቃዎች ለአንደኛ ጊዜ ለመሸጥ በግልፅ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የ2018/19 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ፤
- ተጫራቾች የተጨመሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆኑ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ገዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦሪጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው፤
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ የዋጋ ዝርዝር እና እስፔስፍኬሽን የቀየረ ተቀባይት የለውም፤
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፤
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምር ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ክፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 1ኛ ላይ ላለው ተራ ቁጥር ጨረታ 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው፤
- ያገለገሉ አሮጌ እቃዎች ምትጫረቱ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ ንብረት እና አስተዳደር ክፍል በአካል በመምጣት እቃዎቹን መመልከትና መጫረት ይችላሉ፤
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ18/03/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ያገለገሉ አሮጌ እቃዎች፤ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህክምና እቃዎች ጨረታው የሚከፈተው በ17/03/2019 ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት።
ጨረታ ማስከበሪያ
- 1ኛ ላይ ላለው ተራ ቁጥር 50,000 (ሃምሳ ሺ) ብር በ “CBE, CBO እና በSinqe” ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
- 2ኛ ላይ ላለው ተራ ቁጥር 50,000 (ሃምሳ ሺ) ብር በካሽ ማስያዝ አለባቸው።
- ያገለገሉ አሮጌ እቃዎች፤ ብረታ ብረቶች፤ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የህክምና እቃዎች ያሸነፈው ተጫራች በተከታታይ 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ እቃዎቹን ማንሳት እንዳለበት እያሳወቅን ይህ ካልሆነ ግን ያሲያዘው ብር ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ሆኖ ሌላ ጨረታ የሚወጣ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ