Addis Zemen (Nov 16, 2026)
የተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ
ማስታወቂያ 6/2019
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በቁጥር ገጕወፋ/2270/18 በቀን በ15/07/2018 ዓ.ም በጻፈዉ ደብዳቤ መነሻ ያገለገለ ተሽከርካሪ እና የተለያዩ ጋሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
- ሎት 1፡- ያገለገለ ሃዮንዳይ HYUNDI Fጭነት ተሽከርካሪ፣
- ሎት 2፡- የተለያዩ ጋሪዎችና ብረታ ብረቶች
ስለዚህ በጨረታው መሠዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ፡-
1. ማንኛውም ይህንን ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ጨረታውን ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስለእያንዳንዱ ብር 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 6፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታው ማስከበሪያ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም መሰራት አለበት።
3. የጨረታው አሸናፊ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል።
4. የተሽከርካሪው አይነት ሃዮንዳይ/HYuNDI/ የጭነት፣ ሞዴል 1M4፣ የተመረተበት ሀገር ኮሪያ፣ የተመረተበት አመት እ.ኤ.አ 2007 ሲሆን ተጫራቾች የተሸከርካሪውን ሁኔታ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የጋሪዎችና የብረታ ብረቶች ሁኔታ ለመመልከት ይህ ጨረታ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ/የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ኦሪጂናልና አንድ ፎቶ ኮፒ ዶክመንቶችን ኦሪጂናልና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በሰም ታሽጎ እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኦሪጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
7. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል።
- ማሳሰቢያ፡- ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ የምታቀርቡ 90 ቀንና ከዚያ በላይ የሚቆይ መሆን አለበት።
- ከላይ የተገለፁ ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸውም ግለሰቦች ጨረታውን መሳተፍ ይችላሉ፣
ለበለጠ መረጃ 0113300112/0910027182
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ወልቂጤ