Addis Zemen (Nov 19, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች
ጨረታ ቁጥር 06/2026/27
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም ያገለገሉ የተሽከርካሪ ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ ከተሽከርካሪ የተፈቱ ብረታ ብረቶች፣ የጣሊያን ስሪት ፕላይውድ (ኮምፖርሳቶ)፣ የጀነሬተር መለዋወጫ እቃዎችን እና የኤሌክትሪክ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሁሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል።
1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከህዳር 15 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 29 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የጣሊያን ስሪት ፕላይውድ (ኮምፖርሳቶ)፣ የጀነሬተር ዕቃዎች እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ምድቦች የሚገኙት ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።
3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።
4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።
5. ህዳር 30 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎፋ ሰፈር ቅርንጫፍ የሚገኝበት ህንፃ 2ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል።
6. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ