Be'kur (Nov 23, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1. ስቴሽነሪ
- ሎት 2. ኤሌክትሮኒስ
- ሎት 3. የጽዳት እቃዎች
- ሎት. 4 ናፍጣ እና ቤንዚን ትራንስፖርት
- ሎት 5. የመኪና የሞተር ዘይት እና የጥርሳ ጥርስ ዘይት
- ሎት 6 ጀኔሬተር
- ሎት 7. በርና መስኮት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ።
- የግብር ከፋይ/ቲን ናምበር/ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- በእያንዳንዱ ሎት የዕቃወቹን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1/አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከ14/03/2019 ዓ/ም እስከ 23/03/2019 ዓ/ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ14/03/2019 ዓ/ም እስከ 23/03/2019 ድረስ ማስገባት ይችላል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 24/03/2019 ዓ/ም 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር/በሎት/ድምር ይሆናል።
- ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ወድቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም እና ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈትበት ቀን ጀምሮ 28 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆይል።
- ተጫራቾች የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመዉ ጃ/ወ/መ/ብርሃን ከተማ ባሉት በስድስቱ ፑል ንብረት ክፍል ሲሆን ተጫራቾች ትራንስፖርት እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡ ፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ. 10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት