የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር የቶታል በርሜሎችን ለስድስት (6) ወር በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Nov 25, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር የቶታል በርሜሎችን ለስድስት (6) ወር በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ጨረታውን መጫረት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታውን ሰነድ ሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር ጽ/ቤት በመምጣት የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ከፍሎ በመግዛት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሰባት (7) ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 2:00-10:00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከ2:00-6:00 ሰዓት፤ ከሐሙስ ህዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ የጨረታውን ሰነድ በመውሰድ እቃውን ባለበት ሁኔታ መመልከትና ጨረታውን መወዳደር የሚችል መሆኑን እየገለጽን ጨረታው ዓርብ ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ከረፋዱ 3፡50 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሞኤንኮ ሠራተኞች ማህበር

አድራሻ

ሐያት ሆስፒታል አጠገብ

በተጨማሪ ሙሉ መረጃ በሰነዱ ላይ ተገልጿል።

MOENCO

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *