በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ተንቀሳቃሽ የከባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ የተለያዩ አሮጌ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ሞዴል ተሽከርካሪዎችን አሁን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ተንቀሳቃሽ የከባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ የተለያዩ አሮጌ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ሞዴል ተሽከርካሪዎችን አሁን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 06, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ብ.ማ.ኮ.ግ.ጨ (Disposal)005/2018

በሚድሮክ ኢንቨስትምንት ግሩፕ የብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን ከዚህ በፊት ሲገለገልባቸው የነበሩ በአዲስ አበባ እና በዳለቲ ኳሪ የሚገኙ የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ተንቀሳቃሽ የካባድ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፤ የተለያዩ አሮጌ ማሽኖች እና የተለያዩ አይነት ሞዴል ተሽከርካሪዎችን አሁን ባሉበት ሁኔታ ከዚህ በታች በተገለጸው ዝርዝር መሠረት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  • ሎት 01 –ያገለገሉ አሮጌ የከባድ የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪ ማሽነሪዎች በዳለቲ እና አዲስ አበባ የሚገኙ።
  • ሎት2 ያገለገሉ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎችና ብረታ ብረቶች በዳለቲና አዲስ አበባ የሚገኙ።
  • ሎት3 ያገለገሉ አሮጌ ተሽከርካሪ መኪናዎች አይሱዙ ኤን አር እና አይሱዙ ደብል ካብ በዳለቲ ኳሪ የሚገኙ እና ሚትስቡሺ ደብል ካብ ሲንግል ካብ ቶዮታ፣ አይ ሱዙ ደብል ካብ፣ ላንድሮቨር ቶዮታ፣ አይሱዙ ትሮፐር በአዲስ አበባ የሚገኙ።

በዚህም መሠረት ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆኑ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ሊኖራቸው የሚገባ ሲሆን የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ግለሰብ ከሆኑ ማንነታቸውን ሊገልጽ የሚችል የታደሠ የነዋሪነት መታወቂያ ወይም ፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ለመግዛት ተመላሽ የማይደረግላቸው ለእያንዳንዱ ሎት ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማሰከበሪያ (BID BOND) ብር 50,00.00 (ሃምሣ ሺህ)  CPO ከጨረታ ዶክመንት ጋር በጨረታው መዝጊያው ቀንና ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸውን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለመልካም አፈጻጸም ዋስትና የሚሆን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) ቅድሚያ ማሲያዝና ኮንትራት መፈረም ይኖርባቸዋል።
  6. ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ በመቅረብ ሠነዱን መወስድ ይችላሉ። አድራሻ አዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፊናንስ አካባቢ ጌት ማር ሕንጻ 1 ፎቅ የግዢ መምሪያ ስልክ 09 11 99 70 84/ 09 17 07 36 76/ 09 12 10 25 06
  7. ጨረታው በጨረታው ሠነድ ላይ በተገለፀው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  8. ተጫራቾች ግለሠብ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ትክክለኛ ማንነት የሚገልፅ ፊርማ ከሌለው ሠነዱ ተቀባይነት የማይኖረው ሲሆን ተጫራቾች ድርጅቶች ከሆነ የድርጅቱ ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እያንዳንዱ ዋጋ የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት በፊት መሆን አለበት።
  10. ጨረታው ከተዘጋ በኃላ የሚቀርብ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
  11. ተጫራቾች ንብረቶችን ዘውትር በሥራ ሰዓት ቤንሻንጉል ብሔራዊ ክልል ብልድግሉ ወረዳ በልፀረ ዳላቲ/ ቀበሌ እና አዲስ አበባ በሚገኘው ፋብሪካ በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
  12. ኩባንያው ብሔራዊ ማዕድን ኮርፖሬሽን /የተ/የግ/ኩባንያ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ው።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የብሔራዊ ማዕድን 

ኮርፖሬሽን /የተ/የግ/ኩባንያ