ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የቀለም ሮሎዎች፣ የኤጋ ቆርቆሮ፣ የተለያዩ ወረቀቶች ፕሌቶች እና የመሳሰሉ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የቀለም ሮሎዎች፣ የኤጋ ቆርቆሮ፣ የተለያዩ ወረቀቶች ፕሌቶች እና የመሳሰሉ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Nov 04, 2026)

የተለያዩ ንብረቶች ሽያጭ
ጨረታ ማስታወቂያ

ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪዎች፣ ብረታ ብረቶች፣ የቀለም ሮሎዎች የኤጋ ቆርቆሮ፣ የተለያዩ ወረቀቶች ፕሌቶች እና የመሳሰሉ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርቲፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶችን በአንድ ላይ በፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 11ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
  6. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-
ስልክ ቁጥር፡- 01115 15 50 05/0115 51 88 72
ፋክስ፡- 0115 51 86 96
ፖ.ሳ.ቁጥር:- 2365
ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
አዲስ አበባ
ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *