በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Nov 23, 2026)

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1. ስቴሽነሪ
  • ሎት 2. ኤሌክትሮኒስ
  • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች
  • ሎት. 4 ናፍጣ እና ቤንዚን ትራንስፖርት
  • ሎት 5. የመኪና የሞተር ዘይት እና የጥርሳ ጥርስ ዘይት
  • ሎት 6 ጀኔሬተር
  • ሎት 7. በርና መስኮት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1.  በዘመኑና በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ።
  2.  የግብር ከፋይ/ቲን ናምበር/ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸዉ።
  3.  ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የግብር ክሪላንስ ማቅረብ የሚችሉ።
  4.  የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸዉ።
  5.  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6.  በእያንዳንዱ ሎት የዕቃወቹን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 2 በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1/አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  9.  ጨረታው ከ14/03/2019 ዓ/ም እስከ 23/03/2019 ዓ/ም ድረስ በአየር ላይ ይውላል።
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ14/03/2019 ዓ/ም እስከ 23/03/2019 ድረስ ማስገባት ይችላል።
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጃ/ወ/ ገ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 24/03/2019 ዓ/ም 4፡15 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አይስተጓጎልም፡፡
  12. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር/በሎት/ድምር ይሆናል።
  13. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ወድቅ ይሆናል።
  14. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም እና ስምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  16. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጥራታቸው በባለሙያ ሲረጋገጥ ነው፡፡ ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈትበት ቀን ጀምሮ 28 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆይል።
  17. ተጫራቾች የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመዉ ጃ/ወ/መ/ብርሃን ከተማ ባሉት በስድስቱ ፑል ንብረት ክፍል ሲሆን ተጫራቾች ትራንስፖርት እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡ ፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ. 10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 058 294 00 23 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት