Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች፣ ከክሬን የወረዱ የክሬን መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት፣ ባለ ሶስት ፌዝ ትራንስፎርመር 2000 KWA ከነመለዋወጫዎቹ እና የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን፡–
- ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች
- ከክሬን የወረዱ የክሬን መሳሪያዎች
- ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት
- የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
- ባለ ሶስት ፌዝ ትራንስፎርመር 2000 KWA ከነመለዋወጫዎቹ
ማንኛውም የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሉ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /Ethiopian insurance Corporation/ ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላል። በተጨማሪ የሰሌዳ ቁጥር EX-0109 ኤክስካቫተር ማሽነሪ በአፋር ክልል ሰምሮቢ ወረዳ ዳሊፋጊ አካባቢ ማሽኑ የወደቀበት ቦታ በወንዝ ውስጥ ሲሆን በጨረታ ስለሚሽጥ ተጫራቾች በቦታው ተገኝታችሁ መመልከት ትችላላችሁ። ተጨማሪና አዲስ መረጃ ለማግኘት ሰመራ ቅርንጫፍ ስልክ ቁጥር 09 46-00-10-04 እንዲደውሉ እናሳውቃለን።
ሀ/ የዕቃ ማስያዣ፡– የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው።
ለ/ የተሽከርካሪ ማስያዣ
የጨረታ መነሻ |
እስከ ብር 50,000.00 |
20 በመቶ |
ከብር 50,001.00 |
እስከ ብር 100,000.00 |
ብር 15,000.00 |
ከብር 100,001.00 |
እስከ 200,000.00 |
ብር 25,000.00 |
ከብር 200,001.00 |
እስከ 300,000.00 |
ብር 37,000.00 |
ከብር 300,00100 |
እስከ 400,000.00 |
ብር 50,000.00 |
ከብር 400,001.00 |
እስከ 500,000.00 |
ብር 60,000.00 |
ከብር 500,00100 |
እስከ 800,000.00 |
ብር 75,000.00 |
ከብር 800,001.00 |
ብር በላይ |
ብር 100,000.00 |
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሃር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው ጥቅምት 04 ቀን 2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል። በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ተጫራቾች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ክፍያ ፈጽመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይከፍላሉ።
ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆነ ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ መንሳት አለበት።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 439-2589 እና 011 439-2545 መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት