አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል 12 ተሽከርካሪዎችን እና 4 የመኪና ጋቢናዎች፣ የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (ቅሪተ አካሎች)፣ በቁጥር 1,369 መፅሀፎች፣ 10 ቴሌቪዥኖች እና 2 የተባይ መርጫ ሲሊንደር/ጋን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 20, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል 12 ተሽከርካሪዎችን እና 4 የመኪና ጋቢናዎች፤ የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (ቅሪተ አካሎች) ፣ በቁጥር 1,369 መፅሀፎች፣10 ቴሌቪዥኖች እና 2 የተባይ መርጫ ሲሊንደር/ጋን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

1. የመኪናዎቹን/ንብረቶቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ11ሰዓት ድረስ ተሸከርካሪዎቹን/ንብረቶቹን ቀጥሎ በተጠቀሱት አድራሻዎች በስራ ሰዓት ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አፍሪካ ኢንሹራንስ ጉዳት የደረሰባቸው ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቦታ፣ ቃሊቲ ኖክ ማደያ በሚድሮክ ተርሚናል ወደ ውስጥ 15 ኪሜ ገባ ብሎ የተጎዱ ተሽከርካሪዎች ማቆሚያ ቅጥር ግቢ ውስጥ፤

2.  ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀው እና የተሽከርካሪዎቹን/ንብረቶቹን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22 ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ NB ቢዝነስ ሴንተር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይቻላል።

3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን እያንዳንዱን ተሸከርካሪ / ንብረት ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ 22 ካራማራ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ NB ቢዝነስ ሴንተር 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605  ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ተሸከርካሪ/ ንብረት የመነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (C.P.O) ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይህን መስፈርት የማያሟላ ተጫራች ወዲያውኑ ከጨረታው ይሰረዛል’ ተጫራቹ በጨረታው ከተሸነፈ በማስያዣ ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ የሚጫረቱበት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

6. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ስም ከፍለው እንዲወስዱ ይደረጋል’ ግዥውን ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የማይፈቀድ መሆኑን እየገለጽን ይህ ካልሆነ ግን አሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከቢሪያ (C.P.O) በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።

7. ጨረታው ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ቦሌ አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ ዋና መ/ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።

8. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ / ንብረት ሙሉ ክፍያ 15% VAT ጨምሮ በ 7 የስራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል’ ሙሉ ክፍያ ፈጽመው በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሱ ለአስር ተከታታይ ቀናት በየቀኑ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ የማቆሚያ ቦታ ኪራይ የምናስከፍል ሲሆን በ 10 ቀናት ውስጥ ካላነሱ ግን ያስያዙት ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነታቸው ይሰረዛል።

9. ለጨረታ በቀረቡት ተሸከርካሪዎች / ንብረቶች ላይ የሚፈለጉ የስም ማዛወሪያ፣ ግብርና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል።

10. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-21-89-95፣ 011-6-18-08-43 በመደወል ወይንም ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በግንባር ቀርቦ መረዳት ይቻላል።

11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ከ እንደራስ ናሽናል ጋር በመተባበር