Your cart is currently empty!
አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ መነፅር እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ኮር መሳይ ብረት፣ ሴራሚክ፣የወዳደቀ ጎማና ድንጋይ፣ ቁራሌ በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 29, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
በጉምሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅ/ጽ/ቤት የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ25/02/2018 እና በ28/02/2018 ዓም በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች፡-
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለ መሆኑ ከልራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸውን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ25/02/2018 እና በ28/02/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
| የጨረታ ቦታ | የጨረታው ዓይነት | ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች | የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ | የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት | 
| ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት | ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ | ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ መነፅር እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ኮር መሳይ ብረት፣ ሴራሚክ፣ የወዳደቀ ጎማና ድንጋይ፣ ቁራሌ | ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ25/02/2018 እና በ28/02/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45 
 | ግልጽ ጨረታ በ25/02/2018 እና በ28/02/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ25/02/2018 እና በ28/02/2018 ዓ.ም. 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ 
 | 
5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ:- በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸነፉ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት