Your cart is currently empty!
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማኀበር ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታሀ
የጨረታ ቁጥር EL-MD-2026_281
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግል ማኀበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
|
የሎት ቁጥር |
ያገለገሉ ዕቃዎች ዝርዝር |
ዕቃው የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ሲፒአ (ብር) |
|
ሎት-1 |
የተለያዩ መጠን ያላቸው ቁርጥራጭ ብረቶችና ቆርቆሮዎች፣ ያገለገሉ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ ጎማዎች፣ በርሜሎች፣ የጋዝ ሲሊንደር፣ የተለያዩ እቃዎች |
ኮምቦልቻ ምግብ ማቀነባበሪያ፤ ኮምቦልቻ
|
200,000.00
|
|
ሎት-2 |
ጀነሬተር፣ የተለያዩ የመኪና ጎማዎች፣ ብረት፣ ሊዝ ማሽን አካል፣ የነዳጅ መቅጃ፣ ቦይለር፣ ድሪል፣ ግራይንደር ማሽን እና የተለያዩ እቃዎች |
መልጌ ወንዶ አግሮ ፕሮሰሲንግ፤ ወንዶ |
200,000.00 |
|
ሎት-3 |
ድሪፕላይኖች፣ የምርት መሰብሰቢያ ክሬቶች፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች እና ፕላስቲኮች |
ኤልፎራ ጂቱ እርሻ–ቢሾፍቱ |
200,000.00 |
|
ሎት-4 |
ንቃይ ቆርቆሮ፣ የብረት ከንች፣ ቱቦ፣ የብረት በር፣ የተለያየ ርዝመት ያላቸው ብረታብረቶች፣ በጣውላ የተሰሩ ከንች |
ድሬዳዋ ቄራ፤ ድሬዳዋ |
100,000.00
|
|
ሎት-5 |
ቁርጥራጭ ብረቶች፣ የተለያዩ ጣውላዎች፣ የተለያዩ የስልክ ቀፎዎች፣ የተለያዩ የጽህፈት መሣሪያዎች |
ጎንደር ቄራ፤ ጎንደር
|
100,000.00
|
1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና ለተጨማሪ እሴትታክስ (VAT) ወይም ተርን ኦቨር ታክስ (TOT) የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ (ላምበረት) አካባቢ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነዱ መግዣ ዋጋ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ነው።
3. ተጫራቾች ዋጋ ከመስጠታቸው በፊት ዕቃዎች በሚገኙበት ከተማ በአካል በመገኘት ማየት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ለጨረታ ማሰከበሪያ /Bid bond/የሚሆን ብር ከላይ የተገለፀውን በእያንዳንዱ ሎት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
5. ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረጋል።
6. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በተራ ቁጥር 1 የተገለፁትን ፎርማሊቲዎች በማሟላት በፖስታ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መለያ ኮድ (ሎት) እና ቦታ በፓስታው ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ እና እሑድን ሳይጨምር ለ8 (ስምንት) ቀናት እስከ ቀኑ 7፡25 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
9. ተጫራቾች በኤልፎራ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ግብይት መምሪያ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታቸውን እንዲያሰገቡ ይደረግና በ8ኛው ቀን 7፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል፤ በዚሁ እለት 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ 8ኛ ፎቅ ጨረታው ይከፈታል።
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና መ/ቤት ግብይት መምሪያ ቢሮ አዲስ አበባ ጉርድ ሾላ (ላምበረት)አካባቢ በሚገኘው ኤልፎራ ህንፃ 4ኛ ፎቅ።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– +251 91 117 2601/+251 09 54 49 53 63/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር