አዋሽ ባንክ አ.ማ ሲጠቀምባቸው የነበረውን የተለያዩ እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ያገለገሉ ንብረቶች የጨረታ ማስታወቂያ

አዋሽ ባንክ አ.ማ ሲጠቀምባቸው የነበረውን 12 ተሽከርካሪዎች በሎት (1) እና በሎት (2) (ጄኔሬተሮች፣ የብር መቁጠሪያ ማሽን፣ መፈተሻ ማሽን፣ የሂሳብ መደመሪያ፣ የዶላር መፈተሻ ማሽን፣ የውሃ ማጣሪያ፣ ታይፕራይተር፣ የሙቀት መለኪያ፣ የአየር ማቀዝቀዣ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣ ፋክስ፣ የወረፋ መጠባበቂያ፣ ቦይለር፣ ቴሌቪዥን፣ ቴፕ ሪከርደር፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ የተለያዩ ጠረጴዛዎች፣ ኤም ሼልተር፣ ዲክሰን ሼልፍ የመጽሐፍ መደርደሪያ፣ ፋይሊንግና ላተራል ካቢኔት፣ ሴኪውሪቲ ፋይሊንግ ካቢኔት፣ የገንዘብ ማስቀመጫ ፋይሊንግ ሣጥን(ካዝና) የኮት መስቀያ፣ መጋረጃ፣ የተለያዩ ባትሪዎች፣ ኤስ፣ ስታብላይዘር፣ የስልክ ቀፎ፣ የጄኔሬተር ቤት፣ የጥበቃ ቤት፣ ብረታ ብረቶች፣ ፍራሽ ካውንተርና እምነበረድ፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የተለያዩ የማስታወቂያ ምልክቶችን እና የኔትዎርክ ኬብሎች) ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

በመሆኑም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከታች የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚቻል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡

1. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር መረጃ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሣብ ቁጥር 01540000544500 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኙን አዋሽ ባንክ ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1 ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 በመቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2017 .. ከቀኑ 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛትና ማስገባት ይችላሉ፣

2. እያንዳንዱ ተጫራች (በሎት 1) ላይ ለተገለጹት ተሽከርካሪዎች በባንኩ የተቀመጠውን የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

3. እያንዳንዱ ተጫራች (በሎት 2) ላይ ለተዘረዘሩት የቢሮ መገልገያ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) በአዋሽ ባንክ አክስዮን ማህበር ስም አሰርቶ ማስገባት ይኖርበታል፣

4. ያለ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፣

5. የጨረታው አሸናፊ የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) 15% ለተሽከርካሪዎቹ የስም ዝውውር እና ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን ይከፍላል፣

6. ንብረቶቹን አሸዋ ሜዳ በሚገኙት የባንኩ መጋዘኖች እንዲሁም ተሽከርካሪዎቹን በተመለከተ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ባንኩ እያስገነባ በሚገኘው ሕንጻ ቅጥር ግቢ በአካል ቀርቦ በጨረታው ሰነድ ላይ በወጣው ፕሮግራም መሠረት መጐብኘት ይቻላል፣

7. ጨረታው ነሐሴ 27 ቀን 2017 .. ከቀኑ 410 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልቻ ሳፎ ሕንጻ 1 ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል የቢሮ ቁጥር M-11 ውስጥ ይከፈታል፣ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመወዳደሪያ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፣

8. የጨረታው አሸናፊ የጨረታው ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ንብረቶቹን መረከብ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለባንኩ ገቢ በማድረግ ጨረታው ይሰረዛል፣

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

10. ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራሪያ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት በስልክ ቁጥር 011 530 3014 / 011 530 3026 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

አዋሽ ባንክ አ.ማ