Addis Zemen (Apr 11, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር /EEP/DS/06/18
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው በሎት በመከፋፈል አቅርቧል፤
ሎት-1- ብረታ ብረቶች፣ ቁርጥራጭ ስክራፕ እና ማሽነሪ፣ ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዋሸ አርባ ከተማ አካባቢ መልካ ሰዲ ፕሮጀከት ጣቢያ ቅጥር ግቢ።
ሎት-2 ለተቋማችን አገልግሎት የማይሰጡ ብረታ ብረት እና የማሽነሪ ስክራፖች፤ ቦታ ደቡብ-1 ሪጅን (ይርጋለም 1ና2 ሳብስቴሽን፣ ሻኪሶ ሳብስቴሽን እና ዲላ ሳብስቴሽን)፣ ሳውዝ ገሪድ ፕሮጀክት (ዋጆፎ ዌር ሃውስ፣ ወላይታ ሰዶ‐2 እና አርባ ምንጭ-2) እና ገዳ ፕሮጅክት (ሞጆ)፤
ሎት-3- አገልግሎት የሰጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ጎማ፤ ቦታ ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ አዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት ዋና መ/ቤት ግቢ፤
ሎት-4- የአገልግሎት ጊዚያቸው ያለፈባቸው ወረቀቶች፤ ቦታ አዲስ አበባ ኮተቤ ብረታ ብረት ዋና መ/ቤት ግቢ፤
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤
ማሳሰቢያ፡ ውድድሩ የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አክሲዮን ማህበር በፈጠሩት የማወዳደሪያ ሲስተም መተግበሪያ https://onelinkto/njnamp መሰረት መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹ ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል፡–
1.በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሠ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል።
2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ ኦከሽን ኢትዮጵያ አክሲየን ማህበር ጋር ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤
4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው።
5. ተወዳዳሪዎች በሎት አንድ እና ሁለት ላይ ለመሳተፍ በብረት አቅላጭ ድርጅትነት የተሰማሩ መሆን የሚያሳይ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ብረታ ብረቶች አሸናፊ የሆኑ አቅላጭ ድርጅቶች እቃዎችን ከገዙ በኋላ በሻጭ ድርጅት እጅ ዕቃዎቹ በነበሩበት ይዘትና ቅርጽ ለሌላ 3ኛ ወገን መሸጥም ሆነ ማስተላለፍ አይቻልም።
7. በሎት አራት የተቀመጠው የአገልግሎት ጊዚያቸው ያለፈባቸው ወረቀቶች መውሰድ የሚቻለው ቆራርጦ ወይም ፈጭቶ ነው።
8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 2,000,000.00 (ሁለት ሚሊዮን)፣ ለሎት ሁለት ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ) ፣ ለሎት ሶስት ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ) እና ለሎት አራት ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።
9. ጨረታው ከ06/08/18 እስከ 21/08/2018 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ይካሄዳል ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታዉን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።
10. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
11. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ክፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤
12. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፤
13. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
14. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55 11/ 011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
15. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልክ ቁጥር 011-558-1424 ወይም 011 558-0649 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የኢትዮያ ኤሌክትሪክ ኃይል