በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚገኙትን አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ የተለያዩ ብረታ ብረት፣ የተለያዩ ይዘታቸውን የለቀቁ ሞተር ሳይክሎች እና ይዘታቸውን ያልለቀቁ ያገለገሉ መኪናዎች እንዲሁም ይዘታቸውን የለቀቁ የእርሻ ትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በደቡብ ምዕ/ኢት/ሕ/ክ/መንግሥት በካፋ ዞን የአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚገኙትን አሮጌ ጎማዎች፣ አሮጌ የተለያዩ ብረታ ብረት፣ የተለያዩ ይዘታቸውን የለቀቁ ሞተር ሳይክሎች እና ይዘታቸውን ያልለቀቁ ያገለገሉ መኪናዎች እንዲሁም ይዘታቸውን የለቀቁ የእርሻ ትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 23, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ምዕ/ኢት///መንግሥት በካፋ ዞን የአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት የሚገኙትን ሎት-1- አሮጌ ጎማዎች ሎት-2 አሮጌ የተለያዩ ብረታ ብረት፣ ሎት-3 የተለያዩ ይዘታቸውን የለቀቁ ሞተር ሳይክሎች እና ሎት-4- ይዘታቸውን ያልለቀቁ ያገለገሉ መኪናዎች እንዲሁም ሎት-5 ይዘታቸውን የለቀቁ የእርሻ ትራክተሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ

  • የጨረታ ሰነድ ከመግዛታቸው በፊት ተሽከርካሪዎቹ እና የተለያዩ ሌሎች አሮጌ ዕቃዎች የሚገኙበትን ሁኔታ በቦታው ቀርቦ ማየት ይችላሉ።
  • ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲዮ ቅርንጫፍ መደበኛ ገቢ አካውንት ቀርቦ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀናት አዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ግዥ ንብ/አስ/ሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው ሎቶች ለሎት-1 እና ለሎት2 ለአሮጌ ጎማና የተለያዩ ብረታ ብረቶች በባንክ የተረጋገጠ CPO & ጥሬ ገንዘብ እና ቼክ ብር 3000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ እና ሎት 3 ይዘታቸውን የለቀቁሞተር ሳይክሎች በባንክ የተረጋገጠ CPO አናጥሬ ገንዘብ እና ቼክ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ ለሎት– 4- ይዘታቸውን ያልለቀቁ ያገለገሉ መኪናዎችን ብር 100,000.00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ ሎቲ 5- ይዘታቸውን የለቀቁ የእርሻ ትራክተሮች በባንክ የተረጋገጠ CPO &ጥሬ ገንዘብ እና ቼክ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ማሰከበሪያ CPO & በጥሬ ገንዘብ እና በቼክ በአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ግዥ ንብ/አስ/ ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ፋይናንሻል የጨረታ ዶክመንት ተገቢውን ሥም እና ስልክ ቁጥር በመፃፍ እና ፊርማ በማሳረፍ እንዲሁም የታደሰ መታወቂያ ካርድ ኮፒ በማያያዝ ለየብቻ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ የተሟላ ሰነድ በተለያዩ በሰም/በሙጫ/ በታሸጉ ፖስታዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ግዥ ንብ/አስ/ በመቅረብ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  • የጨረታው ሳጥን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ይከፈታል።

የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስትጓጉልም።

15 ተከታታይ ቀናት የተባለው ቅዳሜና እሑድ ጨምሮ የሚቆጠር አይደለም።

ተጫራቾች አሠሪው /ቤት ያዘጋጀውን የቴክኒካል ዶክመንት መጠይቅ ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

አሸናፊ ተጫራች ግዢውን ከመፈጸሙ በፊት ክፍያውን ሙሉ በሙሉ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት መደበኛ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000534863881 በማስገባት ሰነዱን ማቅረብ ይኖርበቸዋል።

/ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 17 00 34 00 / 09 17 33 58 95 / 09 93 71 66 52 መጠየቅ ይቻላል

በካፋ ዞን የአዲዮ ወረዳ ፋይናንስ /ቤት