2merkato.com (Apr 24, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር WB/PAF/07/26
ወጋገን ባንክ አ.ማ ከታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩት ለሰጠው ብድር በእዳ ማካካሻነት የያዛቸውን ንብረቶች እና ባንኩ ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪ ፣ሞተር ሳይክሎች እና ቋሚ ንብረቶች አሁን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ሎት-1 ባንኩ ለሰጠው ብድር በዕዳ ማካካሻነት የያዛቸው ንብረቶች
ሀ-ሕንጻ
|
ተ.ቁ |
የንብረቱ ዓይነት |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
ቤቱ/ሕንጻው ያረፈበት ቦታ በካ.ሜ |
ይዞታው ጠቅላላ ስፋት |
|||
|
ከተማ |
ክ/ከተማ |
ቀበሌ/ወረዳ |
የቦታው ልዩ ስም |
|||||
|
1 |
G+4 መኖሪያ ቤት ሕንጻ በግንባታ ላይ የሚገኝ |
አዲስ አበባ |
አቃቂ ቃሊቲ |
01 |
አለም ባንክ አካባቢ |
33,572,504.39 |
ምድር ቤት 207.467 ካ.ሜ ከ 1ኛ እስከ 4ኛ ወለል እያንዳንዱ ወለል 197.54 ካ.ሜ |
250 ካ.ሜ
|
|
2 |
ቅይጥ አገልግሎት B+G+4 ሕንጻ |
አዲስ አበባ |
ለሚ ኩራ |
09 |
ሰሚት አትሌቶች ሰፈር |
58,203,583.42 |
ቤዝመንትና ምድር ቤት145.65 ካ.ሜ ከ 1ኛ እስከ 4ኛ ወለል 169.76 ካ.ሜ ሚዛኒን 48.91 ካ.ሜ እና አቲክስ 142.35 ካ.ሜ |
250ካ.ሜ
|
|
3 |
G+4 መኖሪያ ቤት ጅምር ሕንጻ |
አዲስ አበባ |
ለሚ ኩራ |
04 |
ቦሌ አራብሳ በሻሌ ዉሀ ታንከር |
31,880,425.67 |
167 ካ.ሜ |
250ካ.ሜ
|
|
4 |
G+1 መኖሪያ ቤት ሕንጻ |
አዲስ አበባ |
ቦሌ |
12 |
ቦሌ ቡልቡላ |
19,437,554.75 |
ቤዝመንት 53.71 ምድር ቤት እና 1ኛ ወለል እያንዳንዱ ወለል 78.88 ካ.ሜ ሰርቪስ ቤት ምድር ቤት እና 1ኛ ወለል ላይ እያንዳንዱ ወለል 30.80 ካ.ሜ |
210 ካ.ሜ |
|
5 |
መኖሪያ ቤት ቤዝመንት፣ምድር ቤት እና ሰርቪስ |
አለታ ወንዶ |
|
ጨፌ ቀበሌ |
ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ |
3,707,039.78 |
ቤዝመንት 47.17 ምድር ቤት 110.24 ካ.ሜ ሰርቪስ ቤቱ 36 ካ.ሜ |
474.38 ካ.ሜ |
|
6 |
G+2 ለንግድ የሚያገለግል ሕንጻ |
ሲዳማ ሀገረ ሰላም |
ሁላ ወረዳ |
ሰቻ ቀበሌ 01 |
ማዕድን አካባቢ |
8,775,512.49 |
ምድር ቤት180.33 ካ.ሜ 1ኛ ፎቅ 176.87 2ኛ ፎቅ 162.52 |
414.73 ካ.ሜ |
|
7 |
የንግድ ቤት/መጋዘን |
ሾኔ |
|
አረንቻ |
ሾኔ ገበያ |
4,552,348.43 |
መጋዘን 390.6 ካ.ሜ አዲስ መጋዘን 129.6 ካ.ሜ |
622.6 ካ.ሜ |
|
8 |
G+0 መኖሪያ ቤት |
ጋምቤላ |
ጋምቤላ |
03 |
ዶንቦስኮ አካባቢ |
815,889.88 |
95.71 ካ.ሜ |
400 ካ.ሜ |
|
9 |
G+1 ለንግድ የሚያገለግል ሕንጻ |
ጋምቤላ |
ጋምቤላ |
04 |
መናኃሪያ አካባቢ |
7,966,511.40 |
ምድር ቤት 246.50 ካ.ሜ 1ኛ ወለል 246.50 ካ.ሜ |
2450 ካ.ሜ |
|
10 |
G+0 መኖሪያ ቤት |
ጋምቤላ |
ጋምቤላ |
05 |
ኢሚግሬሽን አካባቢ |
2,669,612.46 |
88.35 ካ.ሜ እና 100.78 ካ.ሜ |
548 ካ.ሜ |
|
11 |
መኖሪያ ቤት/ኮንደሚኒየም |
ወሊሶ |
|
02 |
ኤጀርሳ ቀበሌ ኮንደሚኒየም ሰፈር |
1,069,132.01 |
74.45 ካ.ሜ |
74.45 ካ.ሜ |
|
12 |
መኖሪያ ቤት |
ቡሌ ሆራ |
|
አርዳ ቢያ |
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ አካባቢ |
2,082,184.25 |
171.60 ካ.ሜ |
200 ካ.ሜ |
|
13 |
G+1 መኖሪያ ቤት ግራውንዱ የተጠናቀቀ ሲሆን አንደኛ ፎቅ ከ 50% በላይ የተጠናቀቀ |
ምዕራብ ጉጂ ዞን ፍንጫዋ |
|
ዱግዳ ዳዋ 01 |
ዱግዳ ዳዋ ቂልጣቁፋ |
5,544,917.24 |
193 ካ.ሜ |
504 ካ.ሜ |
|
14 |
G+0 መኖሪያ ቤት |
ምዕራብ ጉጂ ዞን ፍንጫዋ |
|
01 |
ዱግዳ ዳዋ ቂልጣ ቁፋ |
390,943.17 |
64.68 ካ.ሜ |
400 ካ.ሜ |
ለ-ተሽከርካሪዎች እና ያገለገሉ ቸርኬዎች
|
ተ.ቁ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
ሞዴል |
የስሪት ዘመን |
የተሰራበት ኃገር |
የሞተር ጉልበት (ሲሲ) |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
|
1 |
አአ 03-35321 |
ድርብ ተግባር |
RANGER 2.9 |
2005 |
ፎርድ |
2892 ሲሲ |
800,000.00 |
|
2 |
አአ 03-34548 |
ድርብ ተግባር |
RANGER 2.9 |
2005 |
ፎርድ |
2892 ሲሲ |
800,000.00 |
|
3 |
ያገለገሉ የተሸከርካሪ ቸርኬ ብዛት 24 የአንዱ ቸርኬ የመነሻ ዋጋ |
6,000.00 |
|||||
ሎት-2
ሀ-ባንኩ ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎች እና ሞተር ሳይክሎች
|
ተ.ቁ |
የሰሌዳ ቁጥር |
የተሽከርካሪዉ አይነት |
ሞዴል |
የስሪት ዘመን |
የተሰራበት ሀገር |
የሞተር ጉልበት (ሲሲ) |
የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር |
|
1 |
አአ 03-06239 |
አውቶሞቢል ሚትሱቢሺ |
ላንሰር |
2001 |
ሚትሱቢሺ/ጃፓን |
1299 ሲሲ |
550,000.00 |
|
2 |
አአ 03-0067 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
2007 |
ጃፓን ሱዙኪ |
183 ሲሲ |
35,000.00 |
|
3 |
አአ 03-0480 |
ሞተር ሳይክል |
DT175 |
2005 |
ያማሀ ጃፓን |
171 ሲሲ |
35,000.00 |
|
4 |
አአ 03-3215 |
ሞተር ሳይክል |
TS185ER |
2016 |
ጃፓን ሱዙኪ |
183 ሲሲ |
50,000.00 |
|
5 |
አአ 03-0068 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
2007 |
ሱዙኪ ጃፓን |
183 ሲሲ |
35,000.00 |
|
6 |
አአ 03-0071 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
2000 |
ሱዙኪ ጃፓን |
183 ሲሲ |
40,000.00 |
|
7 |
አአ 03-0093 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
2007 |
ሱዙኪ ጃፓን |
183 ሲሲ |
40,000.00 |
|
8 |
አአ 03-0481 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
|
ጃፓን |
183 ሲሲ |
40,000.00 |
|
9 |
አአ 03-0482 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
2007 |
ሱዙኪ ጃፓን |
183 ሲሲ |
40,000.00 |
|
10 |
አአ 03-0488 |
ሞተር ሳይክል |
TS185 |
2007 |
ሱዙኪ ጃፓን |
183 ሲሲ |
35,000.00 |
|
11 |
አአ 03-0810 |
ሞተር ሳይክል |
DT175 |
|
ጃፓን |
175 ሲሲ |
50,000.00 |
|
12 |
አአ 03-3219 |
ሞተር ሳይክል |
TS185ER |
2016 |
ጃፓን ሱዙኪ |
183 ሲሲ |
50,000.00 |
ለ– ባንኩ ቀደም ሲል ሲጠቀምባቸው የነበሩ ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶች
|
1. የኮምፒዩተር እቃዎች |
2. የቢሮ ማሽኖች እና ሌሎችም |
3. ፈርኒቸር |
4. ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና ባትሪ
|
|
ራክ፣ስሪ ኮም (ዲሊንክ) ስዊች፣ሲስኮ ራውተር፣ሲስተም ዩኒት፣ሞኒተር፣ፖስ፣ታሌስ ሴኩሪቲ፣ ቲፒ ሊንክ፣ ሚኒ ኮምፒዩተር (ቲን ክላይንት)፣ ኤልሲዲ እና ሲአርቲ ሞኒተር፣ ስዊች፣ ፓች ፓናል ፣ሰርቨር፣ ሴኩሪቲ ካሜራ እና ሌሎችም |
ሎትሀ- ዩፒኤስ፣ ትልቁና ትንሹ ኢፕሰን ፕሪንተር ፣ ሌዘር ጀት ፕሪንተር፣ ተርማል ፕሪንተር ፣ታሊ ፕሪንተር፣ ስካነር፣ ቼክ ስካነር፣ሲግኔቸር ፓድ፣ ኢሜጅ ካሜራ፣ኤር ኮንዲሽነር፣ቲቪ እና ሌሎችም |
የተለያዩ ዓይነት የእንግዳ እና ተሽከርካሪ ወንበሮች፣ ባለ 3 መቀመጫ ወንበር፣ ኮፊ ቴብል፣ቸስት ኦፍ ድሮወር፣ድሮወር፣ ኮት መስቀያ፣ የኮምፒዩተር ማስቀመጫ፣ኮኔክቲንግ አንግል፣ ፋይሊንግ ካቢኔት ፣ የተለያየ መጠን እና አይነት ያላቸው ጠረጴዛዎች የካውንተር ፍርስራሽ እና አልሙኒየም፣ ቨርቲካል ብላይንድ፣የኮፒና የታይፕ ራይተር ማስቀመጫ፣ የሶርቲንግ ጠረጴዛ፣ ላይት ቦክስ እና ሌሎችም |
|
|
ሎት ለ- የአማርኛ እና እንግሊዝኛ ታይፕ ራይተር፣ ኤሌክትሮኒክ ካልኩሌተር፣የጥበቃ መፈተሻ የብር መቁጠሪያ ማሽን ፣ዶላር ዲቴክተር ኤክስጄንጅ ሬት ቦርድ፣ ፋክስ ማሽን፣ ፎቶኮፒ ማሽን፣ ባይንዲንግ ማሽን እና ሌሎችም |
5. ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማ
|
||
|
ሎት ሐ- ጀነሬተር፣የውሀ ማጣሪያ፣የእሳት ማጥፊያ፣ ስታብላይዘር እና ሌሎችም |
|||
|
ሎት መ– የተለያየ መጠን ያላቸው ካዝና እና ካሽ ቦክስ |
ማሳሰቢያ
1- ተጫራቾች ከየትኛውም የወጋገን ባንክ ቅርንጫፍ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ብር 345.00 (ሶስት መቶ አርባ አምስት ብር) በሒሳብ ቁጥር 0736452410101 በተጫራቹ ስም ገቢ በማድረግ ገቢ የሆነበትን ደረሰኝ በመያዝ የጨረታው ሰነድ የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ መግዛትና መወዳደር ይችላሉ፡፡
2- ተሽከርካሪዎቹ፣ሞተር ሳይክሎቹ እና ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶች የሚገኙት መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የምርት ማስቀመጫ መጋዘን ግቢ ሲሆን አድራሻው ከቃሊቲ የመኪና ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ከ CCRDA አለፍ ብሎ በሚያስገባው መንገድ ከዴልታ ማደያ ፊት ለፊት ነው። ሕንጻዎቹን እና ተሸከርካሪዎቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባንኩ በሚያወጣው መርሐ-ግብር መሰረት ንብረቶቹ የሚገኙበትን ሁኔታ መመልከት የሚችሉ ሲሆን ያገለገሉ ቋሚ ንብረቶች ሚያዝያ 26፣28 እና 29 ቀን 2018 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ቀኑ 9፡30 ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
3- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ንብረቶቹን የሚገዙቡትን ዋጋ ¼ኛ (ሃያ አምስት በመቶ) ለጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በወጋገን ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ከነሙሉ አድራሻቸው እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ወጋገን ሕንጻ 3ኛ ወለል ንብረት አስተዳደር እና ፋሲሊቲስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጫራቹ ስም፣ፊርማ እና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለበት። ከጨረታው ሳጥን መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
4- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመጫረቻ ዋጋ በቀላሉ በሚጠፋ ወይም በእርሳስ መሙላት የለባቸውም። የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት።
5- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፤ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም፡፡
6- ጨረታው ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወጋገን ባንክ አ.ማ. ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻ 9ኛ ወለል በባንኩ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
7- የጨረታው አሸናፊ ከንብረቶቹ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፤ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ የሚታሰብ ግብር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ፣ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙ ወጪዎች፣ውዝፍ ክፍያዎች እና ሌሎች በሕግ የተወሰኑ ወጭዎች የጨረታው አሸናፊ የሚከፈል ይሆናል፡፡
8- የጨረታ አሸናፊ አሸናፊነቱን ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለበት። በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ከፍሎ ንብረቱን የማይረከብ ተጫራች የጨረታው ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
9- በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ማለትም እስከ 3ኛ ደረጃ ያልወጡ የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ በኋላ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ይመለስላቸዋል።
10- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
ስለ ጨረታው አፈጻጸም ዝርዝር ማብራርያ በስልክ ቁጥር 011-5-535342 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
Ras Mekonnen Street, Wegagen Tower P.O.Box: 1018, Addis Ababa, Ethiopia
Website: www.wegagen.com Email: info@wegagen.com SWIFT: WEGAETAA