በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 09, 2026)

የተተው ዕአዎች የሐራጅ ጨረታ

ቁጥር ሐ_34/2018 ጨረታ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠዉ የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመዉ ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተዉ የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣዉ የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀፅ 10 መሠረት የተተዉ ንብረቶችን ማለትም ELEMENT ASSY, WALL TRANSFORMER, JIG SAW WOODEN BLADE, 4G MULTIFUNCTIONAL GPS TRACKER, GPS TRACKER, S5L CAR FUEL LEVEL SENSOR & OTHERS, Different TYPES OF PERFUMES, CLOTHES, MEN SPORT SHOES, SANDLE SHOES,BLANKET, VACCUME FLASK, CLOTH & SHOES, OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND, CHEMICAL MIXING TANK, CHANNEL STEEL, GALVANISED STEEEL PIPE, MEN SPORT SHOE BRAND, HEALD FRAME OR HURNESS FRAME, FIBER CLEANING TOWEL, CHILDRED SPORT SHOES & LADY SPORT SHOES AS WIRE PROFESSIONAL HOTELP SPECFLC TELEPHONE እቃዎች ባሉበት ሁኔታ በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀነ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀነ 5፡30 ድረስ ከሞጆ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገቢ ሂሳቦች ቡድን መግዛት ይቻላል።

2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፣ አዳማና ሞጆ ቅርጫፎች ብቻ መዘጋጀት አለበት።

4. የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ ማንኛውም ተጫራች እስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

5. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም፤ የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

6. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።

7. በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የእሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።

8. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።

9. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት