Addis Zemen (May 10, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በ08/09/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 02-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የጨረታ መስፈርቶች፡–
1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፡ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፡የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ውትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን በ08/09/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክለት ማድረግ ይችላሉ።
3. ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ አንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው አይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልክቻ ቀንበጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ ጽ/ቤት |
ግልፅ ጨረታና ሐራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ፣ ኤሌክትሮኒክስ፡ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ ፌሮ ብረት ቆርቆሮ፣ጥቅል ብረት፣መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች ጠፍታፋ ብረት ላሜራ፡የወዳደቁ ብረቶችና ፕላስቲኮች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች: |
ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ በ08/09/2018 እስከ ከጠዋቱ3:45 |
ለግልፅ ጨረታ በ08/09/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የሀራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ በ08/09/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል። |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡– በቃሊቲ /ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፈ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ውጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ውሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው ማሰከበሪያ ያሰያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት