ሆራይዘን አዲስ ጎማ የተለያዩ እቃዎችን መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሆራይዘን አዲስ ጎማ የተለያዩ እቃዎችን መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Jun 29, 2026)

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/2019

ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

1. የክራሸር ሮለሮች

2. የተለያዩ የብረት ሞልዶች

3. የብረት ኮንቴነሮች

4. ልዩ ልዩ ሽቦዎች

5. ስኮርች ኮምፓወንድ

6. የብረት፣ የፕላስቲክ እና የእንጨት ፓሌቶች

7. የተለያየ መጠን ያላቸው ብላደሮች

8. ያገለገሉ መካኒካል ማሽንስና ስፔርፓርቶች

9. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌትሪክ ገመዶች

10. አገልግሎት መስጠት የሚችሉ የጎማ የውስጥ ላስቲኮች (ከመነዳሪ )

11. የተጋቡ የብረት በርሜሎች

12. የተጋቡ ፕላቲክ በርሜሎች

13. በጥሩ ይዞታ ላይ ያሉ ያገለገሉ ዘይቶች

14. ብረታ ብረቶች

15. እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዕቃዎች

በዚህም መሠረት ፍላጎት ያላቸውን ተጫራቾች በሙሉ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

2. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከኩባንያው የምርት ሽያጭ ቢሮ መግዛት እና እቃዎቹን ማየት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጓቸውን እቃዎች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በግልፅ ሞልተው፤ ሙሉ ስማቸውንና አድራሻቸውን ጽፈው ከፈረሙበት በኋላ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሳሪስ በሚገኘው ዋናው በሽያጭ ቢሮ ፊት ለፊት ባለው የጥበቃ በር ቁጥር 2 ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሣጥኑ በዚሁ እለት ከጥዋቱ 4፡05 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

4. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- ንብረት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ
ስልክ ቁጥር 011-442-1555/234 ወይም 251 97 402 4142 መጠየቅ ይቻላል።
ሆራይዘን አዲስ ጎማ ማ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር