Addis Zemen (Oct 23, 2026)
በጉምሩክ ኮሚሽን
የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሑ-20/2019 ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም AC ADAPTOB HD TV CABLE TV WALL MOUNT LED HIGHBAY LIGHT SKMEI IRON ADULT HAND WATCH! WOODEN DOOR FRAME & WATER PURIFIER OUT DOOR SOLAR STRIGHT LIGHT & STRIGHT LIGHT STAND! LED STRING LIGHTS! RUBBER NAIL FILTER, S/S MANICURE, METAL DECORATIVE & EYE LASH PHOTO COPY MACHINE AND PRINTER ADULT FABRIC CAP, SHOPPING BAG & OTHERS! RECHARGEBLE CAMPING PORTABLE PORTABLE SHOWER! SHOWER WALL TRANSFORMER CHEMICAL MIXING TANK, CHANNEL STEEL, GALVANISED STEEL PIPE: HEALD FRAME FABRIC MICRO FIBER CLEANING TOWEL SINGLE, DOUBLE PORT FACE PLATE & OTHER S/S ARTIFICIAL EARRING & BEARING, SCHOOL BAG, FABRIC ADULT CAP & SUPERMARKET SHELF! CHILDRED SPORT SHOES BRAND & LADYSPORT SHOES BRAND LADY SKIRT, LADY TIGHT & OTHER: VIBRATION ANALYSIS OF CENTERFUGAL BLOWER FAN! ELECTRIC CRANE SCALE HAIR CLIPER, PERFUME & TROUSERI DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER WITHOUT R£]FROGIR£IOR!TWO SIDE COAIED ART PAPER: የስቴሽነሪና ማስታወቂያ እቃዎችና የተሽከርካሪ መለዋወጫ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በመግዛት ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሠነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት ማየት ይቻላል።
2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ። N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪዉ አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰዉ በስተቀር ማንኛዉም እድሜዉ ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ – ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገዉ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላል።
3. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር መሆኑን እናሳውቃለን።
4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ለሁሉም ዕቃዎች 300,000.00 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንከ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ በኦንላይን የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ማስያዝ ይኖርበታል። ተጫራቾች በወረቀት የሚያስይዙ ከሆነ የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODO BRANCH OFFIC በሚል ሊሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
5. የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበትን ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ስለሚካሄድ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች የጨረታዉን ሂደት በቀጥታ (online) መወዳደር ይችላሉ።
6. ተጫራቾች የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
7. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም! የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
8. የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
9. በተራ ቁጥር 07 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
11. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር የስልክ መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55 11/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ወይም 022-236-0190 ደውለው መጠየቅይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት