Your cart is currently empty!
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ቁጥር 031 ፣ 032 ፣ 033 ፣ 034/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግልጽ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት:
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 031/2018 በ06/06/2018 የተለያዩ አልባሳት ፖሊስተር ጨርቅ ጨምሮ፤ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርት፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ሞተር ዘይት፣ ኮስሞቲክስ እና መዋቢያዎች ፣የመሬት ምንጣፎች ፣ የሞባይል ኮፎዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የስፖርት መስሪያዎች፣ አሮጌ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት፣ አርተፊሻል ጌጣጌጥ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የዕይታ መሳረያዎች የተለያዩ መነፅሮች፣ የተለያዩ ምግብ ነክ፣ የእጅ ሰዓቶች እና የተለያዩ ሌሎች ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 032/2018 በ13/06/2018 የተለያዩ አልባሳት ፖሊስተር ጨርቅ ጨምሮ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርት፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ሞተር ዘይት፣ ኮስሞትክስ እና መዋቢያዎች ፣የመሬት ምንጣፎች፤ የሞባይል ቀፎዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የስፖርት መስሬያዎች ፣ አሮጌ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ፣ አርተፊሻል ጌጣጌጥ ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የዕይታ መሳሪያዎች የተለያዩ መነፅሮች፤ የተለያዩ ምግብ ነክ ፣ የእጅ ሰዓቶች እና የተለያዩ ሌሎች ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 033/2018 በ20/06/2018 የተለያዩ አልባሳት ፖሊስተር ጨርቅ ጨምሮ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርት፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ሞተር ዘይት፣ ኮስሞትክስ እና መዋቢያዎች የመሬት ምንጣፎች፣ የሞባይል ቀፎዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የስፖርት መስሪያዎች ፣ አሮጌ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ፣ አርተፊሻል ጌጣጌጥ ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የዕይታ መሳሪያዎች የተለያዩ መነፅሮች፣ የተለያዩ ምግብ ነክ ፣ የእጅ ሰዓቶች እና የተለያዩ ሌሎች ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ ቁጥር 034/2018 በ27/06/2018 የተለያዩ አልባሳት ፖሊስተር ጨርቅ ጨምሮ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች እና ማስዋቢያዎች፣ ጫማዎች፣ ስፔርፓርት፣ የመኪና ጎማ የመኪና ሞተር ዘይት፣ ኮስሞቲክስ እና መዋቢያዎች፣የመሬት ምንጣፎች፣ የሞባይል (ቀፎዎች፣ የፅዳት እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች የተለያዩ የስፖርት መስሪያዎች፣ አሮጌ ቁርጥራጭ ብረታ ብረት ፣ አርተፊሻል ጌጣጌጥ ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የተለያዩ የዕይታ መሳሪያዎች የተለያዩ መነፅሮች፣ የተለያዩ ምግብ ነክ ፣ የእጅ ሰዓቶች እና የተለያዩ ሌሎች ዕቃዎች
ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፦
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆኑን ይጠበቅበታል፡፡
2. ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው::
3. በግልጽ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሪሲት በመውሰድ ዘመትር በስራ ሰአት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰአት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል፤ ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር ቅ/ጽ/ ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም::
4. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ የሚገኘው ግቢ ነው፡፡
5. ለግልጽ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት፡፡
6. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ ለመጫረት ዕቃዎች ለመግዛት ለሚያቀርቡት ዋጋ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ የሞሉትን የጨረታ ሰነድ እና ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማያያዝ በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከጠዋቱ 2:00 ሰአት እስከ 3:45 ድረስ በድረዳዋ ሙድአነኖ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. ጨረታው ከጠዋቱ 3:50 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ጉምሩክ ለጨረታ በተዘጋጀው ቦታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቦታው ሳይ ባይገኙም ጨረታ ሳጥኑ በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፣፣
10. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፤
11. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
12. ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ከፍያውን ፈፅሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
13. ለግልጽ ጨረታ ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ሥም መሞላት አለበት፤
14. ተጫራቹ ዋጋ ለሰጠው የብር መጠን በቁጥር እና በፊደል መፃፍ አለበት ስርዝ ድልዝ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃልን፡፡
15. የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0915460970(0912885746)መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት