Addis Zemen (Sep 02, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት 04/13/2018 እና በ02/01/2019 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላትበጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የጨረታ መስፈርቶች–
- ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸዉን ለታክስ ማዕከሉ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምስክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 04/13/2018 እና በ02/01/2019 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100(አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተዉ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሰም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በሚከተለዉ የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡፡
|
ተቁ |
የጨረታ ቦታ |
የጨረታው አይነት |
ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች |
የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ |
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት
|
ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ |
ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች፣ የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሽነሪ፣ ተሽከርካሪ፣ አመነበረድ ድንጋይ፣ መሰላል ብረቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች |
ለግልፅና ሐራጅ ጨረታ 04/13/2018 እና በ02/01/2019 እስከ ጠዋቱ 3፡45
|
ለግልጽ ጨረታ 04/3/2018 እና በ02/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 04/13/2018 እና በ02/1/2019ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡ |
5. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡– በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል::
6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋስትና ያስያዙት (c.p.) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የስራ ቀናት ዉስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል፡፡
8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበዉ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡
በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ የቀረበ የተሽከርካሪ መረጃ
|
ቁ |
የተሽከርካሪ አይነት |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
ሞዴል |
የስሪት |
የምርት |
የፈረስ |
|
1 |
HYUNDAI TUCSON |
KMHJ381ADGUI085670
|
D4HAEH616328 |
F/R3/50384 |
KOREA
|
2015 |
1997 |
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-224-1402 ደዉለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት