Be'kur (Nov 23, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አማካይነት
- ሎት 1. በወረዳችን ንብረት ክፍል ያሉ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች (ሞተር ሳይክል እና መኪና) እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረት እንዲሸጥላቸው በቁጥር ገ/118/05/19 በቀን 7/03/2019 ዓ/ም፤
- ሎት 2. ለዉሃ አገልግሎት የሚዉል የግንባታ ቁሳቁስ ግዥ እንዲገዛላቸዉ በቁጥር 1167/1/12/19 በቀን 01/03/2019 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ በጠየቁን መሰረት ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጫረት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ የታክስ ክሊራንስ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የእቃው ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየዉ በሎት ይሆናል፡፡
- የግንባታ ማቴሪያሎችን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ከ14/3/2019 ዓ/ም እስከ 23/3/2019 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም የመኪና፣ ሞተር እና ቁርጥራጭ ብረት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 ከህዳር 14/2019 ዓ/ም እስከ ህዳር 28/2019 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የግንባታ ቁሳቁሱን በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ11ኛዉ ቀን ህዳር 24/2019 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን በ4.00 ይከፈታል፡፡
- የመኪና፣ ሞተር እና ቁርጥራጭ ብረት በጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ16ኛዉ ቀን 29/3/2019 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን በ4.00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟላት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፈት ስልጣን አለዉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ማሸነፋቸዉ እና የዉል ስምምነት እንዲፈጽሙ በተገለጸበት ጊዜ ካሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ እና የግንባታ ማቴሪያሉን ምስ/ደ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግና የጫኝና አዉራጅ በተጫራቹ የሚሸፈን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 335 06 32 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የመኪና ሽያጭን በተመለከተ በአካል በመቅረብ በማየት እንዲሁም የሚቀርቡት ተጫራቾች ንግድ ፈቃድ ቢኖረውም ባይኖረውም መሳተፍ የሚችል ሲሆን ካሸነፈ እቃውን ወዲያውኑ ብሩን ከፍሎ መውሰድ የሚችል መሆኑን እያሳሰብን አሸናፊው የሚለየው በሞላው ከፍተኛ ዋጋ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም፡፡
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት